Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 49:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ያዕ​ቆ​ብም ትእ​ዛ​ዙን ለል​ጆቹ ተና​ግሮ በፈ​ጸመ ጊዜ እግ​ሮ​ቹን በአ​ል​ጋው ላይ ዘር​ግቶ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ፣ እግሮቹን በዐልጋው ላይ ሰብስቦ፣ የመጨረሻ ትንፋሹን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ያዕቆብም ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹን በአልጋ ላይ ሰብስቦ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ያዕቆብ ለልጆቹ ትእዛዝ መስጠቱን ካበቃ በኋላ፥ እግሮቹን በመኝታው ላይ ሰብሰብ አድርጎ ጋደም እንዳለ በሞት ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ያዕቆብ ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹ በአልጋው ላይ ሰብስቦ ሞተ ወደ ወገኖቹም ተከማቸ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 49:33
22 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እኔ ወደ ወገ​ኖች እሰ​በ​ሰ​ባ​ለሁ፤ በኬ​ጢ​ያ​ዊው በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ​ችው ዋሻ ከአ​ባ​ቶች ጋር ቅበ​ሩኝ፤ እር​ስ​ዋም በከ​ነ​ዓን ምድር በመ​ምሬ ፊት ያለች፥


አብ​ር​ሃ​ምም መል​ካም ሽም​ግ​ል​ናን ሸም​ግሎ፥ ዘመ​ኑ​ንም ፈጽሞ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


ስማ​ቸው በሰ​ማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅ​በረ በኵ​ርም፥ ሁሉን ወደ​ሚ​ገ​ዛም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ወደ ፍጹ​ማን ጻድ​ቃ​ንም ነፍ​ሳት፥


ዮሴ​ፍም በሚ​ሞ​ት​በት ጊዜ፥ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ መው​ጣት በእ​ም​ነት ዐሰበ፤ ዐጽ​ሙ​ንም ትተው እን​ዳ​ይ​ወጡ አዘዘ።


“ያዕ​ቆ​ብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሞቱ።


እን​ዲ​ህም አለ፤ “አቤቱ፥ እንደ አዘ​ዝህ ዛሬ ባር​ያ​ህን በሰ​ላም ታሰ​ና​ብ​ተ​ዋ​ለህ።


አፈ​ርም ወደ ነበ​ረ​በት ምድር ሳይ​መ​ለስ፥ ነፍ​ስም ወደ ሰጠው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሳይ​መ​ለስ በሥ​ጋም በነ​በ​ረ​በት ጊዜ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይ​ሰጥ ፈጣ​ሪ​ህን አስብ።


ሞት እን​ደ​ሚ​ያ​ጠ​ፋኝ አው​ቃ​ለ​ሁና ለሟ​ችም ሁሉ ማደ​ሪ​ያው ምድር ናትና።


ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተ​ላል፤ ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እን​ግ​ዲህ አይ​ኖ​ርም።


በወ​ራቱ የደ​ረሰ አዝ​መራ እን​ዲ​ሰ​በ​ሰብ፥ የእ​ህሉ ነዶም በወ​ቅቱ ወደ አው​ድማ እን​ዲ​ገባ፥ በረ​ዥም ዕድሜ ወደ መቃ​ብር ትገ​ባ​ለህ።


ያዕ​ቆ​ብም ልጆ​ቹን ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በኋ​ለ​ኛው ዘመን የሚ​ያ​ገ​ኛ​ች​ሁን እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ተሰ​ብ​ሰቡ።


ይስ​ሐ​ቅም ሸም​ግሎ ዕድ​ሜ​ንም ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ፤ ልጆ​ቹም ዔሳ​ውና ያዕ​ቆብ ቀበ​ሩት።


እር​ሱም ከኤ​ው​ላጥ አን​ሥቶ በግ​ብፅ ፊት ለፊት እስ​ከ​ም​ት​ገኝ እስከ ሴይር ባለው ሀገር ኖረ፤ ወደ አሦ​ር​ዮ​ንም ደረሰ፤ እን​ዲ​ህም ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሁሉ ፊት ተቀ​መጠ።


ወደ ሜዳም አወ​ጣ​ውና “ወደ ላይ ወደ ሰማይ ተመ​ል​ከት፤ ልት​ቈ​ጥ​ራ​ቸው ትችል እን​ደ​ሆነ ከዋ​ክ​ብ​ትን ቍጠ​ራ​ቸው። ዘር​ህም እን​ደ​ዚሁ ነው” አለው።


እር​ሻ​ውና በእ​ር​ስዋ ላይ ያለ​ችው ዋሻ ከኬጢ ልጆች የተ​ገዙ ናቸው።”


ዮሴ​ፍም በአ​ባቱ ፊት ወደቀ፤ በእ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ሳመ​ውም።


ኤል​ሳ​ዕም በሚ​ሞ​ት​በት በሽታ ታመመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለ​ቀ​ሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ሰረ​ገ​ላ​ቸ​ውና ፈረ​ሰ​ኛ​ቸው” አለ።


ኤል​ሳ​ዕም ሞተ፤ ቀበ​ሩ​ትም። ከሞ​ዓ​ብም አደጋ ጣዮች በየ​ዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ ወደ ሀገሩ ይገቡ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios