ሐዋርያት ሥራ 24:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዐምስት ቀን በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከአንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚባል ጠበቃ ጋራ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በጳውሎስም ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዥው አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዢው አመለከቱት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአምስት ቀን በኋላ የካህናት አለቃው ሐናንያ ከአንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ሄደ፤ እነርሱም ወደ አገረ ገዥው ወደ ፊልክስ ቀርበው ጳውሎስን ከሰሱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዡ አመለከቱት። |
የአምሳ አለቃውንም፥ የተከበረ አማካሪውንም፥ ጠቢቡንም፥ የአናጢዎቹንም አለቃ፥ አስተዋይ አድማጩንም ያስወግዳል።
አይሁድም በዚህ ሰው ላይ በመሸመቅ የሚያደርጉትን በዐወቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹንም ወደ አንተ እንዲመጡና በፊትህ እንዲፋረዱት አዝዣቸዋለሁ፤ ደኅና ሁን።”
ከዚህም በኋላ ወደ ቂሣርያ ገቡ፤ ወደ አገረ ገዢውም ደረሱ፤ የተላከውንም ደብዳቤ ለአገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳውሎስንም ወደ እርሱ አቀረቡት።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔም ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በማባበልና ነገርን በማራቀቅ የእግዚአብሔርን ትምህርት ላስተምራችሁ የመጣሁ አይደለም።