Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አህ​ያም አም​ጥ​ተው ጳው​ሎ​ስን በዚያ አስ​ቀ​ም​ጠው ወደ ቂሣ​ርያ አገረ ገዢ ወደ ፊል​ክስ እን​ዲ​ወ​ስ​ዱት አዘ​ዛ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ደግሞም ጳውሎስ ተቀምጦበት ወደ አገረ ገዥው ወደ ፊልክስ በደኅና የሚደርስበት ከብት ይዘጋጅ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ጳውሎስንም ወደ አገረ ገዢው ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲያደርሱት የሚያስቀምጡበትን ከብት ያዘጋጁ ዘንድ አዘዛቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ለጳውሎስም ፈረስ አዘጋጁለትና ወደ አገረ ገዥው ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲደርስ አድርጉት” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ጳውሎስንም ወደ አገረ ገዡ ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲያደርሱት የሚያስቀምጡበትን ከብት ያዘጋጁ ዘንድ አዘዛቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 23:24
14 Referencias Cruzadas  

በሌ​ሊ​ትም ተነ​ሣሁ፤ ከእ​ኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ር​ገው ዘንድ በልቤ ያኖ​ረ​ውን ለማ​ንም አላ​ስ​ታ​ወ​ቅ​ሁም፤ ተቀ​ም​ጬ​በት ከነ​በ​ረው እን​ስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እን​ስሳ አል​ነ​በ​ረም።


አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።


ወደ እር​ሱም ቀረበ፤ ቍስ​ሉ​ንም አጋ​ጥሞ አሰ​ረ​ለት፤ በቍ​ስሉ ላይም ወይ​ንና ዘይት ጨመ​ረ​ለት፤ በአ​ህ​ያ​ውም ላይ አስ​ቀ​ምጦ እን​ዲ​ፈ​ው​ሰው የእ​ን​ግ​ዶ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ጠ​ብ​ቀው ወሰ​ደው፤ የሚ​ድ​ን​በ​ት​ንም ዐሰበ።


ጢባ​ር​ዮስ ቄሣር በነ​ገሠ በዐ​ሥራ አም​ስት ዓመት ጴን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ የይ​ሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮ​ድ​ስም በገ​ሊላ የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወን​ድሙ ፊል​ጶ​ስም የኢ​ጡ​ር​ያ​ስና የጥ​ራ​ኮ​ኒ​ዶስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳ​ን​ዮ​ስም የሳ​ብ​ላ​ኒስ አራ​ተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥


እን​ዲህ የም​ትል ደብ​ዳ​ቤም ጻፈ​ለት።


“ከሉ​ስ​ዮስ ቀላ​ው​ዴ​ዎስ፥ ለክ​ቡር አገረ ገዢ ፊል​ክስ፥ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ ቂሣ​ርያ ገቡ፤ ወደ አገረ ገዢ​ውም ደረሱ፤ የተ​ላ​ከ​ው​ንም ደብ​ዳቤ ለአ​ገረ ገዢው ሰጡት፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም ወደ እርሱ አቀ​ረ​ቡት።


በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ከመ​ም​ህ​ራ​ኑና ጠር​ጠ​ሉስ ከሚ​ባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በአ​ገረ ገዢው ዘንድ ከሰ​ሱት።


ሀገረ ገዢ​ውም እን​ዲ​ና​ገር ጳው​ሎ​ስን ጠቀ​ሰው፤ ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስ​ተ​ዳ​ዳሪ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንም ታው​ቃ​ለህ። አሁ​ንም ደስ እያ​ለኝ ክር​ክ​ሬን አቀ​ር​ባ​ለሁ።


“ክቡር ፊል​ክስ ሆይ፥ በዘ​መ​ንህ ብዙ ሰላ​ምን አግ​ኝ​ተ​ናል፤ በጥ​በ​ብ​ህም በየ​ጊ​ዜው በየ​ሀ​ገሩ የሕ​ዝቡ ኑሮ የተ​ሻ​ሻለ ሆኖ​አል፤ ሥር​ዐ​ት​ህ​ንም በሁሉ ዘንድ ስት​መ​ሰ​ገን አግ​ኝ​ተ​ና​ታል።


በእ​ርሱ ዘንድ ብዙ ቀን ከቈዩ በኋላ ፊስ​ጦስ የጳ​ው​ሎ​ስን ነገር ለን​ጉሡ ነገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ፊል​ክስ በእ​ስር ቤት ትቶት የሄደ አንድ እስ​ረኛ ሰው በእ​ዚህ አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos