Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 23:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 “እን​ኪ​ያስ ከሳ​ሾ​ችህ ሲመጡ እን​ሰ​ማ​ሃ​ለን” አለው፤ በሄ​ሮ​ድ​ስም ግቢ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቁት አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 “የአንተን ጕዳይ ከሳሾችህ ሲቀርቡ አያለሁ” አለው። ከዚያም ጳውሎስ በሄሮድስ ግቢ ውስጥ እንዲጠበቅ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 “ከሳሾችህ ደግሞ ሲመጡ እሰማሃለሁ፤” አለው፤ በሄሮድስም ግቢ ውስጥ ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 “ከሳሾችህ ሲመጡ ጉዳይህን እሰማለሁ” አለው። በሄሮድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ እንዲጠበቅም አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ከሳሾችህ ደግሞ ሲመጡ እሰማሃለሁ አለው፤ በሄሮድስም ግቢ ውስጥ ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 23:35
14 Referencias Cruzadas  

ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መዱ ጐተ​ቱት፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም አወ​ጡት፤ ኤር​ም​ያ​ስም በግ​ዞት ቤት አደ​ባ​ባይ ተቀ​መጠ።


ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተሣለቁበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቆጣና ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን በቤተ ልሔምና በአውራጃዋ የነበሩትን፥ ሁለት ዓመት የሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ሕፃናት ሁሉ አስገደለ።


ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፤ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤


በዚያን ጊዜ የገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ውስጥ ወሰዱት፤ ጭፍራውንም ሁሉ ወደ እርሱ አከማቹ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም።


አይ​ሁ​ድም በዚህ ሰው ላይ በመ​ሸ​መቅ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን በዐ​ወ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ላክ​ሁት፤ ከሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ አንተ እን​ዲ​መ​ጡና በፊ​ትህ እን​ዲ​ፋ​ረ​ዱት አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደኅና ሁን።”


በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ከመ​ም​ህ​ራ​ኑና ጠር​ጠ​ሉስ ከሚ​ባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በአ​ገረ ገዢው ዘንድ ከሰ​ሱት።


ሀገረ ገዢ​ውም እን​ዲ​ና​ገር ጳው​ሎ​ስን ጠቀ​ሰው፤ ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስ​ተ​ዳ​ዳሪ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንም ታው​ቃ​ለህ። አሁ​ንም ደስ እያ​ለኝ ክር​ክ​ሬን አቀ​ር​ባ​ለሁ።


አሁ​ንም በእኔ ላይ ነገር ከአ​ላ​ቸው ወደ አንተ ይም​ጡና ይክ​ሰ​ሱኝ።


ፊል​ክስ ግን አይ​ሁድ ከጥ​ንት ጀምሮ የክ​ር​ስ​ቲ​ያ​ንን ወገ​ኖች ሕግና ትም​ህ​ርት እን​ደ​ሚ​ቃ​ወሙ ያውቅ ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም “እን​ኪ​ያስ የሺ አለ​ቃው ሉስ​ዮስ በመጣ ጊዜ ነገ​ራ​ች​ሁን እና​ውቅ ዘንድ እን​መ​ረ​ም​ራ​ለን” ብሎ ቀጠ​ራ​ቸው።


የመቶ አለ​ቃ​ው​ንም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ጠ​ብ​ቀው፥ በሰፊ ቦታም እን​ዲ​ያ​ኖ​ረው፥ እን​ዳ​ያ​ጠ​ብ​በ​ትም፥ ሊያ​ገ​ለ​ግ​ሉት በመጡ ጊዜም ከወ​ዳ​ጆቹ አን​ዱን ስንኳ እን​ዳ​ይ​ከ​ለ​ክ​ል​በት አዘዘ።


እኔም፦ ተከ​ሳሹ በከ​ሳ​ሾቹ ፊት ሳይ​ቆም፥ ለተ​ከ​ሰ​ሰ​በ​ትም ምላሽ ይሰጥ ዘንድ ፋንታ ሳያ​ገኝ ማንም ቢሆን አሳ​ልፎ መስ​ጠት የሮ​ማ​ው​ያን ሕግ አይ​ደ​ለም ብየ መለ​ስ​ሁ​ላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos