Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 24:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከአምስት ቀን በኋላ የካህናት አለቃው ሐናንያ ከአንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚባል ጠበቃ ጋር ወደ ቂሳርያ ሄደ፤ እነርሱም ወደ አገረ ገዥው ወደ ፊልክስ ቀርበው ጳውሎስን ከሰሱ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዐምስት ቀን በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከአንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚባል ጠበቃ ጋራ ወደ ቂሳርያ ወረደ፤ በጳውሎስም ላይ ያላቸውን ክስ ለአገረ ገዥው አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዢው አመለከቱት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በአ​ም​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና​ንያ ከመ​ም​ህ​ራ​ኑና ጠር​ጠ​ሉስ ከሚ​ባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም በአ​ገረ ገዢው ዘንድ ከሰ​ሱት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከአምስት ቀንም በኋላ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ ከሚሉት ከአንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ እነርሱም ስለ ጳውሎስ ለአገረ ገዡ አመለከቱት።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 24:1
15 Referencias Cruzadas  

ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም ከሄድኩ ከዐሥራ ሁለት ቀን እንደማይበልጥ አንተ ራስህ ማረጋገጥ ትችላለህ፤


የካህናት አለቃው ሐናንያ ግን ጳውሎስን አፉን እንዲመቱት በጳውሎስ አጠገብ የቆሙትን ሰዎች አዘዘ።


እዚያም የካህናት አለቆችና አንዳንድ ታላላቅ የአይሁድ ወገኖች በጳውሎስ ላይ ክሳቸውን አቀረቡ፤ “ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም በማስመጣት ለእኛ መልካም ነገር አድርግልን” ሲሉም ለመኑት፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ጳውሎስን በመንገድ ጠብቀው ሊገድሉት ስለ ፈለጉ ነው።


“ከሳሾችህ ሲመጡ ጉዳይህን እሰማለሁ” አለው። በሄሮድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ እንዲጠበቅም አዘዘ።


ይህን ሰው ለመግደል ሤራ እንደ ተደረገ በሰማሁ ጊዜ ወዲያውኑ ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹም በእርሱ ላይ ያላቸውን ክስ በአንተ ፊት እንዲያቀርቡ ነግሬአቸዋለሁ።”


ለጳውሎስም ፈረስ አዘጋጁለትና ወደ አገረ ገዥው ወደ ፊልክስ በደኅና እንዲደርስ አድርጉት” አላቸው።


ሰባቱ ቀን ሊፈጸም ሲቃረብ ከእስያ የመጡ አይሁድ ጳውሎስን በቤተ መቅደስ በማየታቸው ሕዝቡን ሁሉ አሳድመው ያዙት፤


ኃጢአተኞች በጨለማ አድብተው ልበቅኖችን ለመግደል ቀስታቸውን ገትረዋል፤ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋል።


ንግግሬና ስብከቴ በሰብአዊ ጥበብና ንግግር በማሳመር ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ኀይል የተደገፈ ነበር።


ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር የመሰከርኩት የንግግርን ችሎታና የፍልስፍናን ጥበብ በማሳየት አይደለም።


እኔ በኢየሩሳሌም በነበርኩበት ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች የዚህን ሰው ጉዳይ ካመለከቱኝ በኋላ እንድፈርድበት ጠየቁኝ።


በተቀጠረው ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለበሰና በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለሕዝቡ ንግግር አደረገ።


ፈረሰኞቹ ወደ ቂሳርያ በደረሱ ጊዜ ደብዳቤውን ለአገረ ገዥው ሰጡና ጳውሎስን በፊቱ አቀረቡት።


ጳውሎስ ተጠርቶ በመጣ ጊዜ፥ ጠርጠሉስ እንዲህ ሲል ክሱን ጀመረ፤ “ክቡር ፊልክስ ሆይ! በአንተ አማካይነት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ በመልካም አስተዳደርህም ለሕዝባችን መሻሻል ተገኝቶአል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios