ሐዋርያት ሥራ 18:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስክንድርያም የሚኖር፥ ንግግር የሚችልና መጽሐፍን የሚያውቅ አጵሎስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱም የተማረና ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ የተባለ አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የተማረና ጥሩ የአነጋገር ችሎታ ያለው ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ። |
ይህም ዕዝራ ከባቢሎን ወጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአምላኩም የእግዚአብሔር እጅ በእርሱ ላይ ነበረችና ንጉሡ ያሻውን ሁሉ ሰጠው።
ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፥ “ጌታ ሆይ፥ እማልድሃለሁ፤ ትናንት፥ ከትናንት ወዲያ ባሪያህን ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም። እኔ አፌ ኰልታፋ፥ ምላሴም ተብታባ የሆነ ሰው ነኝ።”
የአምሳ አለቃውንም፥ የተከበረ አማካሪውንም፥ ጠቢቡንም፥ የአናጢዎቹንም አለቃ፥ አስተዋይ አድማጩንም ያስወግዳል።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ይህ ምንድነው?” አላቸው፤ እነርሱም እንዲህ አሉት፥ “በእግዚአብሔር ፊትና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በቃሉና በሥራው ብርቱ ነቢይና እውነተኛ ሰው ስለነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፥
ከዚህም በኋላ በሚሸኙት ጊዜ፥ “እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንደገና እመለሳለሁ፤ አሁን ግን የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም ላደርግ እወዳለሁ” አላቸው፤ ከኤፌሶንም በመርከብ ሄደ።
ተሰብስበው ሳሉም በሕዝቡ ሁሉ ፊት አይሁድን በግልጥ እጅግ ይከራከራቸው ነበር፤ ስለ ኢየሱስም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ከመጻሕፍት ማስረጃ ያመጣላቸው ነበር።
የነጻ ወጭዎች ከምትባለው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያ፥ ከቂልቅያና ከእስያ የሆኑ ሰዎችም ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር።
እነሆ፥ እርስ በርሳችሁ፥ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤ እኔ የአጵሎስ ነኝ፤ እኔ የኬፋ ነኝ፤ እኔ የክርስቶስ ነኝ” የምትሉትን እነግራችኋለሁ።
ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስም ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ መላልሼ ማልጄው ነበር፤ አሁን ሊመጣ አልወደደም፤ በተቻለው ጊዜ ግን ይመጣል።
ወንድሞቻችን ሆይ! እኔም፥ አጵሎስም ብንሆን መከራ የተቀበልነው ስለ እናንተ ነው፤ እናንተ እንድትማሩ፥ ከመጻሕፍት ቃልም ወጥታችሁ በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳትታበዩ ነው።
ከሰዎች መካከል “መልእክቶቹ ከባዶችና አስጨናቂዎች ናቸው፤ ሰውነቱ ግን ደካማ ነው፤ ነገሩም ተርታ ነው” የሚሉ አሉና።
በጥበብ ሁሉ እንድትበለጽጉ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ዘንድ ይጽና፤ በመንፈስም ራሳችሁን አስተምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝሙርንና ምስጋናን፥ የቅድስና ማሕሌትንም በልባችሁ በጸጋ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።