Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 4:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ ትና​ንት፥ ከት​ና​ንት ወዲያ ባሪ​ያ​ህን ከተ​ና​ገ​ር​ኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁም። እኔ አፌ ኰል​ታፋ፥ ምላ​ሴም ተብ​ታባ የሆነ ሰው ነኝ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሙሴም እግዚአብሔርን፣ “ጌታ ሆይ፤ ቀድሞም ሆነ፣ አንተ ከባሪያህ ጋራ ከተነጋገርህ ወዲህ፣ ከቶ አንደበተ ርቱዕ ሰው አይደለሁም። እኔ ኰልታፋና ንግግር የማልችል ሰው ነኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሙሴም ጌታን፦ “ጌታ ሆይ፥ እኔ አንደበተ ርቱዕ አይደለሁም፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባርያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፌንና ምላሴን ይይዘኛል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “እባክህ ጌታ ሆይ፥ ወደዚያ አትላከኝ፤ ቀድሞም ሆነ ወይም አሁን አንተ ከእኔ ጋር መነጋገር ከጀመርክበት ጊዜ አንሥቶ የመናገር ችሎታ የለኝም፤ እኔ አንደበቴ የሚኮላተፍና አጥርቼ ለመናገር የማልችል ነኝ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ጌታ ሆይ! እኔ አፌ ኮልታፋ ምላሴም ጸያፍ የሆነ ሰው ነኝ፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባሪያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም።”

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 4:10
11 Referencias Cruzadas  

እኔም፥ “ወዮ​ልኝ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እነሆ ሕፃን ነኝና እና​ገር ዘንድ አል​ች​ልም” አልሁ።


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል? እኔም አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ተና​ገረ።


እኔ በአ​ነ​ጋ​ገሬ አላ​ዋቂ ብሆ​ንም በዕ​ው​ቀት ግን እን​ዲሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ሁሉን በሁሉ እገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ሙሴም የግ​ብ​ፅን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በሚ​ና​ገ​ረ​ውና በሚ​ሠ​ራ​ውም ሁሉ ብርቱ ሆነ።


ሙሴም መለሰ፥ “እነሆ፥ ባያ​ም​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ባይ​ሰሙ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ህም’ ቢሉኝ ምን እላ​ቸ​ዋ​ለሁ?” አለ።


ከሰ​ዎች መካ​ከል “መል​እ​ክ​ቶቹ ከባ​ዶ​ችና አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ናቸው፤ ሰው​ነቱ ግን ደካማ ነው፤ ነገ​ሩም ተርታ ነው” የሚሉ አሉና።


“በእ​ር​ግጥ እና​ንተ ዓይ​ነ​ተ​ኞች ሰዎች ናችሁ፤ ጥበ​ብም በእ​ና​ንተ ዘንድ ትፈ​ጸ​ማ​ለች።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እሄድ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው።


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ እኔ አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል?” አለ።


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios