Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 18:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በዚህ ጊዜ የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱም የተማረና ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የእስክንድርያ ተወላጅ የሆነ አጵሎስ የተባለ አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱ ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የተማረና ጥሩ የአነጋገር ችሎታ ያለው ሰው ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በእ​ስ​ክ​ን​ድ​ር​ያም የሚ​ኖር፥ ንግ​ግር የሚ​ች​ልና መጽ​ሐ​ፍን የሚ​ያ​ውቅ አጵ​ሎስ የሚ​ባል አንድ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ወደ ኤፌ​ሶን መጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በወገኑም የእስክንድርያ ሰው የሆነ ነገር አዋቂ የነበረ አጵሎስ የሚሉት አንድ አይሁዳዊ ሰው ወደ ኤፌሶን ወረደ፤ እርሱም በመጻሕፍት እውቀት የበረታ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 18:24
22 Referencias Cruzadas  

ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ።


ወንድሞች ሆይ! ስለ አንዱ በሌላው ላይ አንዳችሁም እንዳትታበዩ “ከተጻፈው አትለፍ፤” የሚለውን በእኛ እንድትማሩ፥ በዚህ ስለ እናንተ ስል ራሴንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ ተናገርሁ።


ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ደግሞ፥ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር፤ እርሱ ግን አሁን ለመምጣት አልፈለገም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።


እኔ የምለው፥ እያንዳንዳችሁ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤” “እኔስ የአጵሎስ ነኝ፤” “እኔ ግን የኬፋ ነኝ፤” “እኔስ የክርስቶስ ነኝ፤” ትላላችሁ።


የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና በእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤


የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤


አንዳንዶች “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ሰውነቱ ሲታይ ግን ደካማ ነው፤ ንግግሩም የተናቀ ነው፤” ይላሉ።


የመቶ አለቃውም በዚያ ወደ ኢጣሊያ የሚሄድ የእስክንድርያውን መርከብ አግኝቶ ወደ እርሱ አገባን።


ሙሴም የግብጾችን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ።


እርሱም “ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ ነው፤


እርሱም “ስለዚህ የመንግሥተ ሰማያት ደቀመዝሙር የሆነ ጸሐፊ ሁሉ ከመዝገቡ አዲሱንና አሮጌውን የሚያወጣ ባለቤትን ይመስላል፤” አላቸው።


የአምሳ አለቃውንና ባለ ማዕረጉን፤ አማካሪውንና ጠቢቡን የእጅ ባለሙያ፤ ብልኁንም ምትሀተኛ ይነሣል።


“ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ ለሰማያት አምላክ ሕግ ጸሐፊ ለካህኑ ዕዝራ፤ አሁንም


ይህ ዕዝራ ከባቢሎን መጣ፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ለሙሴ በሰጠው ሕግ ችሎታ ያለው ጸሐፊ ነበረ፤ የአምላኩ የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ስለ ነበረች ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።


ሙሴም ጌታን፦ “ጌታ ሆይ፥ እኔ አንደበተ ርቱዕ አይደለሁም፤ ትናንት ከትናንት ወዲያ ባርያህንም ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፌንና ምላሴን ይይዘኛል።”


ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ ከመጻሕፍት እየገለጠ ለአይሁድ በሁሉ ፊት በጽኑ ያስረዳቸው ነበርና።


ወደ ኤፌሶንም በደረሱ ጊዜ እነዚያን ከዚያ ተዋቸው፤ ራሱ ግን ወደ ምኵራብ ገብቶ ከአይሁድ ጋር ይነጋገር ነበር።


ነገር ግን ሲሰናበታቸው “የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም አደርግ ዘንድ ይገባኛል እግዚአብሔር ቢፈቅድ ግን ወደ እናንተ ደግሞ እመለሳለሁ፤” አላቸው። ከኤፌሶንም በመርከብ ተነሣ።


አጵሎስም በቆሮንቶስ ሳለ ጳውሎስ በላይኛው አገር አልፎ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ አንዳንድ ደቀ መዛሙርትንም አገኘ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios