Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ስለ ወን​ድ​ማ​ችን ስለ አጵ​ሎ​ስም ከወ​ን​ድ​ሞች ጋር ወደ እና​ንተ እን​ዲ​መጣ መላ​ልሼ ማል​ጄው ነበር፤ አሁን ሊመጣ አል​ወ​ደ​ደም፤ በተ​ቻ​ለው ጊዜ ግን ይመ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ደግሞ፣ ከወንድሞች ጋራ ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር፤ እርሱ ግን አሁን ለመምጣት አልፈለገም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ደግሞ፥ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር፤ እርሱ ግን አሁን ለመምጣት አልፈለገም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወንድማችን አጵሎስ ከሌሎች ወንድሞች ጋር እናንተን እንዲጐበኛችሁ በጥብቅ ለምኜው ነበር፤ ነገር ግን እርሱ አሁን ወደ እናንተ ለመምጣት አልፈቀደም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ግን ከወንድሞቹ ጋር ወደ እናንተ ሊሄድ እጅግ አድርጌ ለምኜው ነበር፤ ዛሬም ለመምጣት ከቶ ፈቃድ አልነበረውም፥ ሲመቸው ግን ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 16:12
12 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ፥ “እኔ የጳ​ው​ሎስ ነኝ፤ እኔ የአ​ጵ​ሎስ ነኝ፤ እኔ የኬፋ ነኝ፤ እኔ የክ​ር​ስ​ቶስ ነኝ” የም​ት​ሉ​ትን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


እን​ግ​ዲህ ጳው​ሎስ ምን​ድን ነው? አጵ​ሎ​ስስ ምን​ድን ነው? እነ​ር​ሱስ በቃ​ላ​ቸው የአ​መ​ና​ችሁ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠው ነው።


ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ፥


ጳው​ሎ​ስም ቢሆን፥ አጵ​ሎ​ስም ቢሆን፥ ጴጥ​ሮ​ስም ቢሆን፥ ዓለ​ምም ቢሆን፥ ሕይ​ወ​ትም ቢሆን፥ ሞትም ቢሆን፥ ያለ​ውም ቢሆን፥ የሚ​መ​ጣ​ውም ቢሆን ሁሉ የእ​ና​ንተ ነው።


በእ​ስ​ክ​ን​ድ​ር​ያም የሚ​ኖር፥ ንግ​ግር የሚ​ች​ልና መጽ​ሐ​ፍን የሚ​ያ​ውቅ አጵ​ሎስ የሚ​ባል አንድ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ወደ ኤፌ​ሶን መጣ።


እር​ሱም ስለ ጽድ​ቅና ስለ ንጽ​ሕና፥ ስለ​ሚ​መ​ጣ​ውም ኵነኔ በነ​ገ​ራ​ቸው ጊዜ በዚህ የተ​ነሣ ፊል​ክስ ፈራና ጳው​ሎ​ስን፥ “አሁ​ንስ ሂድ፤ በተ​መ​ቸ​ኝም ጊዜ ልኬ አስ​ጠ​ራ​ሃ​ለሁ” አለው።


ሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና


ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።


ከዚ​ህም በኋላ አጵ​ሎስ በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሳለ፥ ጳው​ሎስ ላይ ላዩን ሄዶ ወደ ኤፌ​ሶን መጣ፤ በዚ​ያም ጥቂት ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትን አገኘ።


ሕግ አዋቂውን ዜማስንና አጵሎስን ምንም እንዳይጎድልባቸው በጉዞአቸው ተግተህ እርዳ።


ሲላስ ግን በዚያ ሊቈይ ወደደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios