Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከሰ​ዎች መካ​ከል “መል​እ​ክ​ቶቹ ከባ​ዶ​ችና አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ናቸው፤ ሰው​ነቱ ግን ደካማ ነው፤ ነገ​ሩም ተርታ ነው” የሚሉ አሉና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አንዳንዶች፣ “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ነገር ግን ሰውነቱ ሲታይ ደካማ፣ ንግግሩም የተናቀ ነው” ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አንዳንዶች “መልእክቶቹ ከባድና ጠንካራ ናቸው፤ ሰውነቱ ሲታይ ግን ደካማ ነው፤ ንግግሩም የተናቀ ነው፤” ይላሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ምናልባት አንዳንዶች “የጳውሎስ መልእክቶች ከባዶችና ብርቱዎች ናቸው፤ እርሱ ራሱ ከእኛ ጋር ሲሆን ግን ደካማ ነው፤ ንግግሩም የተናቀ ነው” ይሉ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 መልእክቶቹስ ከባድና ኃይለኛ ናቸው፥ ሰውነቱ ግን ሲታይ ደካማ ነው፥ ንግግሩም የተናቀ ነው ይላሉና።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 10:10
13 Referencias Cruzadas  

ክር​ስ​ቶስ ወን​ጌ​ልን ለመ​ስ​በክ እንጂ ለማ​ጥ​መቅ አል​ላ​ከ​ኝ​ምና፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስን መስ​ቀ​ሉን ከንቱ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ ነገ​ርን በማ​ራ​ቀቅ አይ​ደ​ለም።


እኔ በአ​ነ​ጋ​ገሬ አላ​ዋቂ ብሆ​ንም በዕ​ው​ቀት ግን እን​ዲሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን ሁሉን በሁሉ እገ​ል​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ ትና​ንት፥ ከት​ና​ንት ወዲያ ባሪ​ያ​ህን ከተ​ና​ገ​ር​ኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይ​ደ​ለ​ሁም። እኔ አፌ ኰል​ታፋ፥ ምላ​ሴም ተብ​ታባ የሆነ ሰው ነኝ።”


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ጳው​ሎስ በእ​ና​ንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆ​ንሁ፥ ከእ​ና​ንተ ብርቅ ግን የም​ደ​ፍ​ራ​ችሁ በክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ቸር​ነት እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፥ በፍ​ቅ​ራ​ችሁ እታ​መ​ና​ለ​ሁና።


ሰዎች በጥ​በ​ባ​ቸው በማ​ያ​ው​ቁት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ስን​ፍና በሚ​መ​ስ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ያመ​ኑ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወድ​ዶ​አ​ልና።


እኔም፥ “ወዮ​ልኝ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እነሆ ሕፃን ነኝና እና​ገር ዘንድ አል​ች​ልም” አልሁ።


ነገር ግን በመ​ል​እ​ክ​ቶች የማ​ስ​ፈ​ራ​ራ​ችሁ እን​ዳ​ይ​መ​ስ​ላ​ችሁ፥ ይህን ትም​ክ​ሕ​ቴን እተ​ወ​ዋ​ለሁ።


ነገር ግን ይህን ነገር የሚ​ና​ገር ይህን ይወቅ፤ በሌ​ለ​ን​በት ጊዜ በመ​ል​እ​ክ​ታ​ችን እንደ ተገ​ለ​ጠው እንደ ቃላ​ችን፥ ባለ​ን​በ​ትም ጊዜ በሥ​ራ​ችን እን​ዲሁ ነን።


እኛ እንደ ደካ​ሞች መስ​ለን እንደ ነበ​ርን፥ ይህን በው​ር​ደት እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ነገር ግን ማንም በሚ​ደ​ፍ​ር​በት እኔ ደግሞ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


ክር​ስ​ቶስ በእኔ አድሮ እን​ደ​ሚ​ና​ገር ማስ​ረጃ ትሻ​ላ​ች​ሁና፤ እር​ሱም ሁሉ የሚ​ቻ​ለው ነው እንጂ፥ በእ​ና​ንተ ዘንድ የሚ​ሳ​ነው የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios