እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።
ሐዋርያት ሥራ 13:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጉባኤውም በተፈታ ጊዜ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ከተመለሱት ከደጋጉ ሰዎች ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ጸጋ ይድኑ ዘንድ እያስረዱ ነገሯቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጉባኤው ከተበተነ በኋላም፣ ብዙ አይሁድና ወደ ይሁዲ ሃይማኖት ገብተው በመንፈሳዊ ነገር የበረቱ ሰዎች፣ ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሏቸው፤ እነርሱም አነጋገሯቸው፤ በእግዚአብሔርም ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ መከሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉባኤውም ከተፈታ በኋላ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ገብተው ከሚያመልኩ ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፤ እነርሱም ሲነግሩአቸው በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ አስረዱአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምኲራቡ ጉባኤ በተበተነ ጊዜ ብዙ የአይሁድ ወገኖችና ወደ አይሁድ እምነት ገብተው እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ሰዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፤ ጳውሎስና በርናባስም ሰዎቹን በማስተማር በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ አሳሰቡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጉባኤውም ከተፈታ በኋላ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ገብተው ከሚያመልኩ ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፥ እነርሱም ሲነግሩአቸው በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ አስረዱአቸው። |
እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ።
በደረሰ ጊዜም የእግዚአብሔርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍጹም ልባቸውም በእግዚአብሔር ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው።
አይሁድ ግን እግዚአብሔርን የሚፈሩ የከበሩ ሴቶችንና የከተማውን ሽማግሌዎች አነሳሡአቸው፤ በጳውሎስና በበርናባስ ላይም ስደትን አስነሡ፤ ከሀገራቸውም አባረሩአቸው።
የደቀ መዛሙርትንም ልቡና አጽናኑ፤ በሃይማኖትም እንዲጸኑ፦“ በብዙ ድካምና መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል” እያሉ መከሩአቸው።
በጌታም ፊት ደፍረው እያስተማሩ፥ እርሱም የጸጋውን ቃል ምስክር እያሳየላቸው፥ በእጃቸውም ድንቅ ሥራና ተአምራትን እያደረገላቸው ብዙ ወራት ኖሩ።
በመካከላቸውም ቀይ ሐር የምትሸጥ ከትያጥሮን ሀገር የመጣች እግዚአብሔርን የምትፈራ አንዲት ሴት ነበረች፤ እግዚአብሔርም ልቡናዋን ከፍቶላት ነበርና ጳውሎስ የሚያስተምረውን ታዳምጥ ነበር፤ ስምዋም ልድያ ይባል ነበር።
ስለዚህም በምኵራብ አይሁድንና እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ ሁልጊዜም በገበያ የሚያገኛቸውን ሁሉ ይከራከራቸው ነበር።
አምነው የተከተሉት ሰዎችም ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ከአርዮስፋጎስ ባለሥልጣኖች ወገን የሚሆን ዲዮናስዮስ ነበር፤ ደማሪስ የምትባል ሴትም ነበረች፤ ሌሎችም አብረዋቸው ነበሩ።
ከእነርሱና ከደጋጎች አረማውያንም ብዙ ሰዎች፥ ከታላላቆች ሴቶችም ጥቂቶች ያይደሉ አምነው ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ሆኑ።
ከዚህም በኋላ ወደ እርሱ የሚመጡበትን ቀን ቀጠሩትና ብዙዎች ወዳረፈበት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥዋትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየመሰከረ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ኦሪትና ከነቢያት እየጠቀሰ ነገራቸው።
ይህም ነገር በእነርሱ ዘንድ የተወደደ ሆነ፤ ሃይማኖቱ የቀናና መንፈስ ቅዱስ ያደረበትን ሰው እስጢፋኖስን፥ ፊልጶስን፥ ጵሮኮሮስን፥ ኒቃሮናን፥ ጢሞናን፥ ጰርሜናን፥ ወደ ይሁዲነት የተመለሰውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።
ኀጢአትም ሞትን እንደ አነገሠችው እንዲሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን ለዘለዓለም ሕይወት ታነግሠዋለች።
እግዚአብሔርን መፍራት ዐውቀን ሰዎችን እናሳምናለን፤ ለእግዚአብሔር ግን እኛ የተገለጥን ነን፤ እንዲሁም በልቡናችሁ የተገለጥን እንደ ሆን እንታመናለን።
ከእርሱም ጋር አብረን እየሠራን፥ የተቀበላችኋትን የእግዚአብሔር ጸጋ ለከንቱ እንዳታደርጓት እንማልዳችኋለን።
አሁንም የተወደዳችሁና የምናፍቃችሁ ወንድሞቻችን ሆይ፥ ደስታችንና አክሊላችን ናችሁ፤ ወዳጆቻችን ሆይ፥ እንዲህ ቁሙ፤ በጌታችንም ጽኑ።
እንግዲህ ከሰማችሁት ከሰማይ በታች በመላው ዓለም ከተሰበከው እኔ ጳውሎስም አዋጅ ነጋሪና መልእክተኛ ሆኜ ከተሾምሁለት፥ ከወንጌል ትምህርት ተስፋ የመሠረታችሁ አቅዋም ሳይናወጥ ጨክናችሁ በሃይማኖት ብትጸኑ፥
እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን ፍጹም የሚሆነውን ሰው እናቀርበው ዘንድ፥ እኛ የምናስተምርለት፥ ሰውን ሁሉ ወደ እርሱ የምንጠራለትና የምንገሥጽለት፥ ሥራውንም በጥበብ ሁሉ የምንናገርለት ነው።
አስተውሉ፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ የሚያቃልል አይኑር፤ ሕማምን የምታመጣ፥ ብዙዎችንም የምታስታቸውና የምታረክሳቸው መራራ ሥር የምትገኝበትም አይኑር።
ሌላ ልዩ ትምህርት አታምጡ፤ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።
እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ።