ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።”
2 ሳሙኤል 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አኪጦፌልም አቤሴሎምን፥ “ቤት ሊጠብቁ ወደ ተዋቸው ወደ አባትህ ቁባቶች ግባ፤ እስራኤልም ሁሉ አባትህን እንዳሳፈርኸው ይሰማሉ፤ ከአንተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃቸው ይበረታል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አኪጦፌልም ለአቤሴሎም መልሶ፣ “ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ አባትህ ከተዋቸው ቁባቶቹ ጋራ ግባና ተኛ፤ ከዚያም አንተ፣ አባትህን እጅግ የጠላህ መሆንህን መላው እስራኤል ይሰማና ዐብሮህ ያለው ሁሉ ክንዱ ይበረታል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አኪጦፌልም መልሶ፥ “ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ አባትህ ከተዋቸው ዕቁባቶቹ ጋር ግባና ተኛ፤ ከዚያም አንተ፥ አባትህን እጅግ የጠላህ መሆንህን መላው እስራኤል ይሰማና አብሮህ ያለው ሁሉ ክንዱ ይበረታል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አኪጦፌልም አቤሴሎምን እንዲህ አለው፦ “ቤት እንዲጠብቁ ከተዋቸው ከአባትህ ቁባቶች ጋር ተገናኝ በዚህም እስራኤላውያን ሁሉ አባትህን እንዳዋረድከው ያውቃሉ፤ ከአንተም ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ ስሜታቸው ይበረታታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አኪጦፌልም አቤሴሎምን፦ ቤት ሊጠብቁ ወደ ተዋቸው ወደ አባትህ ቁባቶች ግባ፥ እስራኤልም ሁሉ አባትህን እንዳሳፈረኸው ይሰማሉ፥ ከአንተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃቸው ይበረታል አለው። |
ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።”
ወደ እርስዋም አዘነበለ፥ “እባክሽ ወደ አንቺ ልግባ አላት፤” እርስዋ ምራቱ እንደ ሆነች አላወቀም ነበርና። እርስዋም፥ “ወደ እኔ ብትገባ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው።
በእነዚያም ወራት ረዓይት በምድር ላይ ነበሩ። ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፤ እነርሱም በዱሮ ዘመን ስማቸውን ያስጠሩ ኀያላን ሰዎች ሆኑ።
የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤትህ ክፉ ነገርን አስነሣብሃለሁ፤ ሚስቶችህንም በዐይኖችህ እያየህ እወስዳለሁ፤ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፤ በዚችም ፀሐይ ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።
ኢዮናዳብም አለው፦“ ታምሜአለሁ ብለህ በአልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህም ሊያይህ ይመጣል፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ የምበላውን እንጀራ እንድትሰጠኝ፥ መብሉንም እኔ እያየሁ እንድታበስልልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላው እለምንሃለሁ በለው።”
አሁንም ጌታችሁ ሳኦል ሞቶአልና እጃችሁ ትጽና፤ እናንተም በርቱ፤ የይሁዳም ቤት በእነርሱ ላይ ንጉሥ እሆን ዘንድ ቀብተውኛል።”
ዳዊትም ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤቱ መጣ፤ ንጉሡም ቤቱን ሊጠብቁ የተዋቸውን ዐሥሩን ቁባቶች ወስዶ ለጠባቂ ሰጣቸው፤ ቀለብም ሰጣቸው፤ ነገር ግን ወደ እነርሱ አልገባም፤ በቤትም ተዘግተው እስኪሞቱ ድረስ መበለቶች ሆነው ተቀመጡ።
በሰሎሞንም ዘመን ሁሉ የእስራኤል ጠላት ነበረ። አዴርም ያደረጋት ክፋት ይህች ናት፤ እስራኤልን አስጨነቀ በኤዶምያስም ነገሠ።
እርሱም፥ “ፊቱን አይመልስብሽምና፥ ሱነማዪቱን አቢሳን ይድርልኝ ዘንድ ለንጉሡ ለሰሎሞን እንድትነግሪው እለምንሻለሁ” አለ።
ንጉሡም ሰሎሞን ለእናቱ መልሶ፥ “ሱነማዪቱን አቢሳን ለአዶንያስ ለምን ትለምኚለታለሽ? ታላቅ ወንድሜ ነውና መንግሥትን ደግሞ ለምኚለት፤ ካህኑም አብያታርና የሶርህያ ልጅ የጭፍሮች አለቃ ኢዮአብ ደግሞ ከእርሱ ጋር ናቸው” አላት።
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ አድናችኋለሁ፥ በረከትም ትሆናላችሁ፣ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።
በእናንተ ላይ ዝሙት ይሰማል፤ እንደዚህ ያለው ዝሙትም አረማውያን እንኳ የማያደርጉት ነው፤ ያባቱን ሚስት ያገባ አለና።
እስራኤልም ሁሉ ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግሞም እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ዘንድ እንደ በረቱ ሰሙ፤ ሕዝቡም ደንፍተው ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልጌላ ተሰበሰቡ።
አንኩስም፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ዘንድ እጅግ የተጠላ ሆኖአል፤ ስለዚህም ለዘለዓለም ባሪያ ይሆነኛል” ብሎ ዳዊትን አመነው።