Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 15:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ንጉ​ሡና ከእ​ር​ሱም በኋላ ቤተ ሰቡ ሁሉ በእ​ግ​ራ​ቸው ወጡ፤ ንጉ​ሡም ቁባ​ቶቹ የነ​በሩ ዐሥ​ሩን ሴቶች ቤቱን ይጠ​ብቁ ዘንድ ተወ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ንጉሡ ከመላው ቤተ ሰቡ ጋራ ወጣ፤ ቤተ መንግሥቱንም እንዲጠብቁ ዐሥር ቁባቶች አስቀረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ ካስቀራቸው ዐሥር ዕቁባቶች በቀር፥ ንጉሡም እርሱንም ተከትለው መላው ቤተሰቡ ሸሹ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህ ንጉሡ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቁለት ዘንድ ካስቀራቸው ዐሥር ቊባቶች በቀር ቤተሰቡንና መኳንንቱን ሁሉ በማስከተል ሸሽቶ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ንጉሡም ከእርሱም በኋላ ቤተ ሰቡ ሁሉ ወጡ፥ ንጉሡም አሥሩን ሴቶች ቁባቶቹን ቤቱን ይጠብቁ ዘንድ ተወ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 15:16
12 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ምንኛ በዙ! በእኔ ላይ የሚ​ቆ​ሙት ብዙ ናቸው።


ዳዊ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ቤቱ መጣ፤ ንጉ​ሡም ቤቱን ሊጠ​ብቁ የተ​ዋ​ቸ​ውን ዐሥ​ሩን ቁባ​ቶች ወስዶ ለጠ​ባቂ ሰጣ​ቸው፤ ቀለ​ብም ሰጣ​ቸው፤ ነገር ግን ወደ እነ​ርሱ አል​ገ​ባም፤ በቤ​ትም ተዘ​ግ​ተው እስ​ኪ​ሞቱ ድረስ መበ​ለ​ቶች ሆነው ተቀ​መጡ።


ይህን ዓለም አት​ም​ሰሉ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም አድሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ደ​ውን መል​ካ​ሙ​ንና እው​ነ​ቱን፥ ፍጹ​ሙ​ንም መር​ምሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤ​ትህ ክፉ ነገ​ርን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ እያ​የህ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለዘ​መ​ድ​ህም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ችም ፀሐይ ፊት ከሚ​ስ​ቶ​ችህ ጋር ይተ​ኛል።


አቤ​ግ​ያም ፈጥና ተነ​ሣች፤ በአ​ህ​ያም ላይ ተቀ​መ​ጠች፤ አም​ስ​ቱም ገረ​ዶ​ችዋ ተከ​ተ​ሉ​አት፤ የዳ​ዊ​ት​ንም መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተከ​ትላ ሄደች፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው።


አሁ​ንም ባሪ​ያህ ወደ ጌታዬ ያመ​ጣ​ች​ውን ይህን መተ​ያያ ተቀ​በል፤ በጌ​ታ​ዬም ዘንድ ለሚ​ቆሙ ሰዎች ስጣ​ቸው።


ባር​ቅም ዛብ​ሎ​ን​ንና ንፍ​ታ​ሌ​ምን ወደ ቃዴስ ጠራ​ቸው፤ ዐሥር ሺህም ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ወጡ፤ ዲቦ​ራም ከእ​ርሱ ጋር ወጣች።


የን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች ንጉ​ሡን፥ “እነሆ፥ ጌታ​ችን ንጉሥ የመ​ረ​ጠ​ውን ሁሉ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ እና​ደ​ር​ጋ​ለን” አሉት።


ንጉ​ሡና ሕዝቡ ሁሉ በእ​ግር ወጡ፤ በሩ​ቅም ቦታ ቆሙ።


ባለ​ጠ​ጋ​ውም እጅግ ብዙ የበ​ግና የላም መንጋ ነበ​ረው።


በላ​ያ​ችን ላይ የቀ​ባ​ነው አቤ​ሴ​ሎ​ምም በጦ​ር​ነት ሞቶ​አል፤ አሁ​ንም ንጉ​ሡን ለመ​መ​ለስ ስለ​ምን ዝም ትላ​ላ​ችሁ?” አሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቃል ወደ ንጉሥ ደረሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios