በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ታስቈጡኝ ዘንድ ትታችሁኛልና፥ ለሌሎች አማልክትም ዐጥናችኋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።
1 ነገሥት 9:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውም ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ፦ እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ? ብሎ ይደነቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ቤተ መቅደስ አሁን እጅግ የሚያስደንቅ ቢሆንም እንኳ፣ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይገረማል፤ እያፌዘም፣ ‘እግዚአብሔር በዚህች ምድርና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ያደረገው ስለ ምን ይሆን?’ ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ ከፍ ከፍ ብሎ የሚታየው ቤተ መቅደስ ፈርሶ የፍርስራሽ ክምር ይሆናል፤ በዚያ በኩል የሚያልፉ ሰዎች ይህን አይተው በመደንገጥ ‘እግዚአብሔር ይህን አገርና ይህን ቤተ መቅደስ ለምን እንዲህ አደረገ?’ በማለት ይሳለቁበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፍ ከፍ ብሎ የነበረው ይህ ቤት ባድማ ይሆናል፤ በዚያም የሚያልፍ ሁሉ እያፍዋጨ ‘እግዚአብሔር በዚህ አገርና በዚህ ቤት ስለምን እንዲህ አደረገ?’ ብሎ ይደነቃል። |
በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ታስቈጡኝ ዘንድ ትታችሁኛልና፥ ለሌሎች አማልክትም ዐጥናችኋልና ቍጣዬ በዚህ ስፍራ ላይ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።
የንጉሡም የአበዛዎች አለቃ የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ። የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ።
“ስለዚህም የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ሆነ፤ በዐይናችሁም እንደምታዩ ለድንጋጤና ለመደነቂያ፥ ለመዘበቻም አሳልፎ ሰጣቸው።
የእግዚአብሔርንም ቤተ መቅደስ አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሰ፤ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠለ፤ መልካሙንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፋ።
ከፍ ከፍ ብሎ የነበረውንም ይህን ቤት እያየ በዚያ የሚያልፍ መንገደኛ ሁሉ፦ ‘እግዚአብሔር በዚህ ሀገርና በዚህ ቤት ስለ ምን እንዲህ አደረገ?’ ብሎ ይደነቃል።
“ለዚህም ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፦ ይህን ሁሉ ትልቅ የሆነ ክፉ ነገርን ስለ ምን እግዚአብሔር ተናገረብን? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ኀጢአት ምንድን ነው? ቢሉህ፥
ይህችንም ከተማ ለጥፋትና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ በእርስዋም የሚያልፍ ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነግጣል፤ ያፍዋጫልም።
ኢኮንያን ተዋረደ፤ ለምንም እንደማይጠቅም የሸክላ ዕቃ ሆነ፤ እርሱንና ዘሩን ወደማያውቀው ሀገር ወርውረው ጥለውታልና።
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ፥ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
“ኤዶምያስም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ የሚያልፍባትም ሁሉ ይደነቃል፤ ስለ መጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጭባታል።
እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ፥ “አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለ ምን አደረገብን?” ብትሉ፥ አንተ፥ “እንደ ተዋችሁኝ፥ በሀገራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፥ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ ሀገር ለሌሎች ሰዎች ትገዛላችሁ” ትላቸዋለህ።
ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።
የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ ፥ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፥ በእሳት አቃጠለ።
ሳምኬት። መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፦ “በውኑ የምድር ሁሉ ደስታ፥ አክሊልና ክብር የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ።
ምድርም በሁለንተናዋ ዲንና ጨው፥ መቃጠልም እንደ ሆነባት፥ እንዳይዘራባትም፥ እንዳታበቅልም፥ ማናቸውም ሣርና ልምላሜም እንዳይወጣባት፥ እግዚአብሔር በቍጣውና በመዓቱ እንደ ገለበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፥ እንደ አዳማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥