ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
1 ነገሥት 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አባትህ በጽድቅ፥ በንጹሕ ልብና በቅንነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብትሄድ፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዐቴንም ሕጌንም ብትጠብቅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተም አባትህ ዳዊት እንዳደረገው ሁሉ፣ በልበ ቅንነትና በትክክለኛነት በፊቴ ብትሄድ፣ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትፈጽም፣ ሥርዐቶቼንና ሕጎቼን ብትጠብቅ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት እኔን ብታገለግል፥ የእኔን ሕግና ሥርዓት ብትጠብቅ፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት እኔን ብታገለግል፥ የእኔን ሕግና ሥርዓት ብትጠብቅ፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም አባትህ በየዋህ ልብና በቅንነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብትሄድ፥ ያዘዝሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ሥርዐቴንም ፍርዴንም ብትጠብቅ፥ |
ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርስዋ ደግሞ ራስዋ ወንድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅንነትና በእጄ ንጹሕነት ይህን አደረግሁት።”
ባሪያዬም ዳዊት እንዳደረገ፥ ያዘዝሁህን ሁሉ ብትሰማ፥ በመንገዴም ብትሄድ፥ በፊቴም የቀናውን ብታደርግ፥ ትእዛዜንና ሥርዐቴን ብትጠብቅ፥ ከአንተ ጋር እኖራለሁ፤ ለዳዊትም እንደ ሠራሁለት የታመነ ቤትን እሠራልሃለሁ፤ እስራኤልንም ለአንተ እሰጥሃለሁ።
ከዚህ በኋላ ሰሎሞን በሸመገለ ጊዜ ልቡ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ልብ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር አልነበረም። ከባዕድ ያገባቸው ሚስቶቹም ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን መለሱት።
ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን አልተከተለውም።
ከዳዊትም ቤት፤ መንግሥቱን ከፍዬ ሰጥቼህ ነበር፤ ነገር ግን በፍጹም ልቡ እንደ ተከተለኝ፥ በፊቴም ቅን ነገር ብቻ እንዳደረገ፥ ትእዛዜንም እንደ ጠበቀ እንደ ባሪያዬ እንደ ዳዊት አልሆንህም።
ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።
አባትህም ዳዊት እንደ ሄደ፥ ሥርዐቴንና ትእዛዜን ትጠብቅ ዘንድ በመንገዴ የሄድህ እንደ ሆነ፥ ዘመንህን አበዛልሀለሁ።”
ሰሎሞንም እግዚአብሔርን ይወድድ ነበር፤ በአባቱም በዳዊት ሥርዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮረብታው ላይ ይሠዋና ያጥን ነበር።
ሰሎሞንም አለ፥ “እርሱ በፊትህ በእውነትና በጽድቅ፥ በልብም ቅንነት ከአንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከአባቴ ከባሪያህ ከዳዊት ጋር ታላቅ ቸርነት አድርገሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ ሰጥተህ ታላቁን ቸርነትህን አቈይተህለታል።
“ስለዚህ ስለምትሠራልኝ ቤት በሥርዐቴ ብትሄድ፥ ፍርዴንም ብታደርግ፥ ትመላለስባቸውም ዘንድ ትእዛዞቼን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የነገርሁትን ቃል ከአንተ ጋር አጸናለሁ።
አሁንም የእስራኤል አምላክ አቤቱ፦ አንተ በፊቴ እንደ ሄድህ ልጆችህ በፊቴ ይሄዱ ዘንድ መንገዳቸውን ቢጠብቁ፥ በፊቴ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው ከአንተ አይጠፋም ብለህ ለአባቴ ለዳዊት ተስፋ የሰጠኽውን ጠብቅ።
“አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መልካም ነገርም እንዳደረግሁ አስብ።” ሕዝቅያስም እጅግ አለቀሰ።
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
በትእዛዜም ቢሄድ፥ እውነትንም ለማድረግ ፍርዴን ቢጠብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።
“እንዲህም ይሆናል፤ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ፈጽመህ ብትሰማ፥ ዛሬም ያዘዝሁህን ትእዛዙን ሁሉ ብታደርግ፥ ብትጠብቅም፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከምድር አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል።