Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 17:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን የአ​ባ​ቱን አም​ላክ ፈለገ፤ በአ​ባ​ቱም ትእ​ዛዝ ሄደ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሥራ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ነገር ግን ከእስራኤል ድርጊት ይልቅ፣ የአባቱን ፈለገ፤ ትእዛዞቹንም ተከተለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን የአባቱን አምላክ ፈለገ፥ በትእዛዙም ሄደ፥ እንደ እስራኤልም ያለ ሥራ አልሠራም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ኢዮሣፍጥ የአባቱን አምላክ የእግዚአብሔርን መመሪያ ተከተለ፤ ትእዛዞቹንም ጠበቀ፤ የእስራኤል ነገሥታት ያደርጉት የነበረውንም ዐይነት ክፉ ሥራ ከቶ አልፈጸመም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን የአባቱን አምላክ ፈለገ፤ በትእዛዙም ሄደ፤ የእስራኤልንም ሥራ አልሠራም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 17:4
21 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም ተማ​ከረ፤ ሁለ​ትም የወ​ርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መው​ጣት ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡ​አ​ችሁ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ እነሆ” አላ​ቸው።


ይህም ኀጢ​አት ሆነ፥ ሕዝቡ በዳን ወዳ​ለች ወደ አን​ዲቱ ጣዖት ይሄዱ ነበ​ርና።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በልቡ ባሰ​በው ቀን ወደ ሠራው መሠ​ዊያ ወጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዓል አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም ሊሠዋ ወጣ።


ሰሎ​ሞ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይወ​ድድ ነበር፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ሥር​ዐት ይሄድ ነበር፤ ነገር ግን በኮ​ረ​ብ​ታው ላይ ይሠ​ዋና ያጥን ነበር።


ዳዊ​ትም አባ​ትህ በጽ​ድቅ፥ በን​ጹሕ ልብና በቅ​ን​ነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብት​ሄድ፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሕጌ​ንም ብት​ጠ​ብቅ፥


ይሁ​ዳም ደግሞ እስ​ራ​ኤል ባደ​ረ​ጋት ሥር​ዐት ሄደ እንጂ የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ አል​ጠ​በ​ቀም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉት።


የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።


በይ​ሁ​ዳም ምሽ​ጎች ከተ​ሞ​ችን ሠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕረ​ፍት ስለ ሰጠው ምድ​ሪቱ ጸጥ ብላ ነበር፤ በዚ​ያም ዘመን ጦር​ነት አል​ነ​በ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ ጋር ነበረ፤ በፊ​ተ​ኛ​ዪ​ቱም በአ​ባቱ በዳ​ዊት መን​ገድ ሄዶ​አ​ልና፥ ጣዖ​ት​ንም አል​ፈ​ለ​ገ​ምና፤


ከነ​ቢ​ዩም ከኤ​ል​ያስ እን​ዲህ የሚል ጽሕ​ፈት መጣ​በት፥ “የአ​ባ​ትህ የዳ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በአ​ባ​ትህ በኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ መን​ገድ፥ በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአሳ መን​ገድ አል​ሄ​ድ​ህ​ምና፥


አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም ፈለ​ገው፤ በሰ​ማ​ር​ያም እየ​ታ​ከመ ሳለ አገ​ኙት፤ ወደ ኢዩም አመ​ጡት፤ እር​ሱም ገደ​ለው፦ እነ​ር​ሱም፥ “በፍ​ጹም ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የፈ​ለ​ገው የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ነው” ብለው ቀበ​ሩት። ከአ​ካ​ዝ​ያ​ስም ቤት ማንም መን​ግ​ሥ​ትን ይይዝ ዘንድ የሚ​ችል አል​ነ​በ​ረም።


ኢዮ​አ​ታ​ምም በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መን​ገ​ዱን አቅ​ን​ቶ​አ​ልና በረታ።


አባ​ቱም ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሄደ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ለም።


እስ​ራ​ኤል ሆይ! አንተ አላ​ዋቂ አት​ሁን፤ አን​ተም ይሁዳ! ወደ ጌል​ጌላ አት​ሂድ፤ ወደ ቤት​አ​ዊ​ንም አት​ውጡ፤ በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አት​ማሉ።


ሁለ​ቱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድ​ቃን ነበሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐ​ትና በት​እ​ዛ​ዙም ሁሉ ያለ ነውር የሚ​ሄዱ ነበሩ።


እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችሁማለን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos