1 ነገሥት 20:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ቃል ስለ አክዓብ ወደ ባሪያው ወደ ኤልያስ መጣ፤ እግዚአብሔርም አለው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርም ሰው ወጥቶ ለእስራኤል ንጉሥ፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሶርያውያን እግዚአብሔር የኰረብታ እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም ብለዋልና ይህን ስፍር ቍጥር የሌለው ሰራዊት በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤ አንተም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃለህ’ ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ሶርያውያን ጌታ የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም’ ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃላችሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ’ ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም “አክዓብ በፊቴ እንደ ተዋረደ አየህን? በፊቴ የተዋረደ ስለ ሆነ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመጣለሁ እንጂ፥ በእርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላመጣም፤” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ቴስብያዊው ወደ ኤልያስ መጣ። |
እነሆም፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮርብዓምም መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።
እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
ነቢዩ ኤልያስም ወደ ሰማይ አቅንቶ ጮኸ፤ እንዲህም አለ፥ “አቤቱ፥ የአብርሃምና የይስሐቅ የእስራኤልም አምላክ ሆይ፥ ስማኝ፤ ጌታዬ ሆይ፥ ዛሬ በእሳት ስማኝ፤ አንተ በእስራኤል ላይ አምላክ እንደ ሆንህ፥ እኔም ባሪያህ እንደ ሆንሁ፤ ይህንም ሥራ ስለ አንተ እንዳደረግሁ እነዚህ ሕዝቦች ይወቁ።
ሁለቱም የዐመፅ ልጆች የሆኑ ሰዎች ገብተው በፊቱ ቆሙ፤ “እግዚአብሔርንና ንጉሡን ሰድበሃል” ብለው መሰከሩበት። የዚያ ጊዜም ከከተማ አውጥተው በድንጋይ ደብድበው ገደሉት።
“አክዓብ በፊቴ እንደ ደነገጠ አየህን? በፊቴ በልጁ ዘመን በቤቱ ላይ ክፉ ነገር አመጣለሁ እንጂ በእርሱ ዘመን ክፉ ነገር አላመጣም።”
“የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፤ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።”
ለእኔም ሕዝብ እንድትሆኑ እቀበላችኋለሁ፤ አምላክም እሆናችኋለሁ፤ እኔም ከግብፃውያን ባርነት ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ግብፃውያንም እጄን በግብፅ ላይ በዘረጋሁ ጊዜ፥ የእስራኤልንም ልጆች ከመካከላቸው በአወጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
በዚያም ቀን የምድር ሁሉ አምላክ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፥ በዚያ የውሻ ዝንብ እንዳይሆን ሕዝቤ የሚቀመጥባትን የጌሤምን ምድር እለያለሁ።
አቤቱ! ኀጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኀጢአት ሠርተናልና ኀጢአታችን ተቃውሞናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ።
በትእዛዜ አልሄዳችሁምና፥ ፍርዴንም አላደረጋችሁምና፥ በዙሪያችሁም እንደሚኖሩት እንደ አሕዛብ ሕግ አድርጋችኋል።”
በሚሄዱባቸውም አሕዛብ መካከል ርኵሰታቸውን ሁሉ ይናገሩ ዘንድ ከሰይፍና ከራብ፥ ከቸነፈርም ጥቂቶች ሰዎችን ከእነርሱ አስቀራለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
ነገር ግን በመካከላቸው በአሉ፥ ከግብጽም ምድር አወጣቸው ዘንድ በፊታቸው በተገለጥሁላቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።
ይህን የሠራሁ ስለ እናንተ እንዳይደለ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ስለ መንገዳችሁ እፈሩና ተዋረዱ።
ቅዱሱም ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ይታወቃል፤ ቅዱሱንም ስሜን ከእንግዲህ ወዲህ አላረክስም፤ አሕዛብም የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር፥ እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
እጄንም እዘረጋባቸዋለሁ፤ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዴብላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ እንጀራ አልበላችሁም፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክረውን መጠጥም አልጠጣችሁም።
ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አላደረገም እንዳይሉ፥ በቍጣ ጠላት ሆኑኝ።