Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እነ​ሆም፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከይ​ሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ኢዮርብዓም መሥዋዕት ለማቅረብ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ፣ በእግዚአብሔር ቃል ታዝዞ አንድ የእግዚአብሔር ሰው ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ኢዮርብዓም መሥዋዕት ለማቅረብ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ በጌታ ትእዛዝ የተላከ አንድ ነቢይ እነሆ ከይሁዳ መጥቶ እዚያ ደረሰ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢዮርብዓም መሥዋዕት ለማቅረብ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የተላከ አንድ ነቢይ እነሆ ከይሁዳ መጥቶ እዚያ ደረሰ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ኢዮርብዓምም ዕጣን እያጠነ በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ፥ እነሆም፥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው በእግዚአብሔር ቃል ከይሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 13:1
23 Referencias Cruzadas  

“ይህ የማ​የው የተ​ቀ​በረ ነገር ምን​ድን ነው?” አለ የዚ​ያ​ችም ከተማ ሰዎች፥ “ከይ​ሁዳ መጥቶ በቤ​ቴል መሠ​ዊያ ላይ ይህን ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ነገር የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መቃ​ብር ነው” ብለው ነገ​ሩት።


በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤


“ከይ​ሁዳ ንጉሥ ከአ​ሞጽ ልጅ ከኢ​ዮ​ስ​ያስ ከዐ​ሥራ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእ​ነ​ዚህ በሃያ ሦስቱ ዓመ​ታት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ማልጄ ተነ​ሥቼ ተና​ገ​ር​ኋ​ችሁ፤ ነገር ግን አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝም።”


ይችን ከተማ የሚ​ወጉ ከለ​ዳ​ው​ያን ይመ​ጣሉ፤ ከተ​ማ​ዋ​ንም በእ​ሳት ያነ​ድ​ዱ​አ​ታል፤ ያስ​ቈ​ጡ​ኝም ዘንድ በሰ​ገ​ነ​ታ​ቸው ላይ ለበ​ዓል ያጠ​ኑ​ባ​ቸ​ውን፥ ለሌ​ሎ​ችም አማ​ል​ክት የመ​ጠ​ጥን ቍር​ባን ያፈ​ሰ​ሱ​ባ​ቸ​ውን ቤቶች ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።


በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ ሄደው ወደ​ሚ​ያ​ጥ​ኑ​ላ​ቸው፥ በመ​ከ​ራ​ቸው ጊዜ ከቶ ወደ​ማ​ያ​ድ​ኗ​ቸው አማ​ል​ክት ይጮ​ኻሉ።


ንጉ​ሡ​ንም ዖዝ​ያ​ንን እየ​ተ​ቃ​ወሙ፥ “ዖዝ​ያን ሆይ፥ ዕጣን ማጠን ለተ​ቀ​ደ​ሱት ለአ​ሮን ልጆች ለካ​ህ​ናቱ ነው እንጂ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታጥን ዘንድ ለአ​ንተ አይ​ገ​ባ​ህም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርቀ​ሃ​ልና ከመ​ቅ​ደሱ ውጣ፤ ይህም በአ​ም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ለአ​ንተ ክብር አይ​ሆ​ን​ህም” አሉት።


የቀ​ረ​ውም ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው የሰ​ሎ​ሞን ነገር በነ​ቢዩ በና​ታን ታሪክ፥ በሴ​ሎ​ና​ዊ​ውም በአ​ኪያ ትን​ቢት፥ ስለ ናባ​ጥም ልጅ ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባየው በባለ ራእዩ በኢ​ዩ​ሔል ራእይ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?


በቤ​ቴል ባለው መሠ​ዊያ ላይ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ከተ​ሞች ውስጥ ባሉት በኮ​ረ​ብ​ታ​ዎቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የተ​ና​ገ​ረው ነገር በእ​ው​ነት ይደ​ር​ሳ​ልና።”


ያም ከመ​ን​ገድ የመ​ለ​ሰው ነቢይ ያን ሰምቶ፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ላይ ያመፀ ያ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ነው” አለ።


እን​ጀ​ራም አት​ብላ፤ ውኃም አት​ጠጣ፤ በመ​ጣ​ህ​በት መን​ገ​ድም አት​መ​ለስ ሲል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃሉ አዝ​ዞ​ኛ​ልና” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሰጠው ምል​ክት መሠ​ዊ​ያው ተሰ​ነ​ጠቀ፤ በው​ስ​ጡም ያለው ስብ ፈሰሰ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ሳማያ እን​ዲህ ሲል መጣ።


እንደ ቆሬና ከእ​ር​ሱም ጋር እንደ ተቃ​ወ​ሙት ሰዎች እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከአ​ሮን ልጆች ያል​ሆነ ሌላ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እን​ዳ​ይ​ቀ​ርብ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ቃል እንደ ተና​ገ​ረው፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ብላ​ቴ​ና​ውም፥ “እነሆ፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በዚ​ህች ከተማ አለ፤ እር​ሱም የተ​ከ​በረ ሰው ነው፤ የሚ​ና​ገ​ረው ሁሉ በእ​ው​ነት ይፈ​ጸ​ማል፤ አሁ​ንም ወደ​ዚያ እን​ሂድ፤ ምና​ል​ባት የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገድ ይነ​ግ​ረ​ና​ልና” አለው።


ደግ​ሞም በቤ​ቴል ኮረ​ብታ የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ያሳተ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ያሠ​ራ​ውን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገጃ፥ ይህ​ንም መሠ​ዊ​ያና መስ​ገጃ አፈ​ረሰ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱ​ንም አቃ​ጠ​ለው።


ነገር ግን በበ​ረታ ጊዜ ለጥ​ፋት ልቡ ታበየ፤ አም​ላ​ኩ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደለ፤ በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ ገባ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በግ​ብፅ በፈ​ር​ዖን ቤት ባሪ​ያ​ዎች ሳሉ ለአ​ባ​ትህ ቤት ተገ​ለ​ጥሁ፤


ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።


አሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ አንተ፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትን​ቢት አት​ና​ገር፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ቤት አት​ዘ​ብ​ዝ​ባ​ቸው ብለ​ሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios