1 ነገሥት 12:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ኀጢአት ሆነ፥ ሕዝቡ በዳን ወዳለች ወደ አንዲቱ ጣዖት ይሄዱ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም አድራጎት ኀጢአት ሆነ፤ ሕዝቡም በዚያ ላለው ለመስገድ እስከ ዳን ድረስ ርቆ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቹም እስከ ዳን ድረስ በጣዖቱ ፊት ተሰልፈው ሄዱ፤ በዚህም ሁኔታ ጣዖትን በማምለክ ኃጢአት ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹም እስከ ዳን ድረስ በጣዖቱ ፊት ተሰልፈው ሄዱ፤ በዚህም ሁኔታ ጣዖትን በማምለክ ኃጢአት ሠሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአንዱ ጥጃ ይሰግድ ዘንድ ሕዝቡ እስከ ዳን ድረስ ይሄድ ነበርና ይህ ኀጢአት ሆነ። |
አንድ ነቢይም ወደ እስራኤል ንጉሥ መጥቶ፥ “የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር በሚመጣው ዓመት ይመጣብሃልና፥ በርታ፤ የምታደርገውንም ዕወቅ” አለው።
ኢዩ ግን በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ይሄድ ዘንድ አልተጠነቀቀም፤ እስራኤልንም ካሳተው ከኢዮርብዓም ኀጢአት አልራቀም።
እስራኤልም ከዳዊት ቤት ተለዩ፤ የናባጥንም ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን ከመከተል እስራኤልን መለሰ፤ ታላቅም ኀጢአት አሠራቸው።
የእስራኤል ኀጢአት የሆኑት የአዎን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾህና አሜከላም በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ፤ ተራሮችንም፥ “ክደኑን፤ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን” ይሉአቸዋል።