1 ነገሥት 16:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 የቀረውም ዘንበሪ ያደረገው ነገር፥ የሠራውም ጭከና፥ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ ነው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም27 ሌላው ዖምሪ በዘመኑ የፈጸመው፣ ያደረገውና ያከናወነው ሁሉ በእስራኤል የነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን? Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 ዖምሪ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉና ያከናወነውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ዖምሪ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉና ያከናወነውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 የቀረውም ዖምሪ ያደረገው ነገር፥ የሠራውም ጭከና፥ በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን? Ver Capítulo |
ዘንበሪም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በሰማርያም ቀበሩት፤ ልጁም አክአብ በፋንታው ነገሠ። 28 ‘ሀ’ ዘንበሪም ዐሥራ አንድ ዓመት ሲሆነው የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ ነገሠ። በነገሠም ጊዜ ሠላሳ አምስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ አምስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጋዙባ የምትባል የሴላህ ልጅ ነበረች። 28 ‘ለ’ በአባቱም በአሳ መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ጽድቅን ያደርግ ዘንድ ከእርስዋ ፈቀቅ አላለም። በተራሮች የነበሩትንም አማልክት አላስወገደም፤ ሕዝቡም በተራሮቹ ይሠዉላቸውና ያጥኑላቸው ነበረ። 28 ‘ሐ’ ኢዮሳፍጥም ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የሠራው፥ የተዋጋውና ያደረገው ኀይል ሁሉ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ ነው። 28 ‘መ’ በአባቱም በአሳ ዘመን የነበረውን ርኵሰት ሁሉ ከምድር አስወገደ። በኤዶምም ንጉሥ አልነበረም። 28 ‘ሠ’ ንጉሥ ኢዮሳፍጥም ወርቅና ብርን ሊያመጡለት ወደ አፌር ይልክ ዘንድ በተርሴስ መርከብ አሠራ፤ በጋስዮንጋቤር የነበረችው መርከብ ተሰብራለችና አልሄደችም። 28 ‘ረ’ የእስራኤልም ንጉሥ አካዝያስ ኢዮሳፍጥን፥ “አገልጋዮችህንና አገልጋዮቼን በመርከብ እንላክ” አለው። ኢዮሳፍጥም እንቢ አለ። 28 ‘ሰ’ ኢዮሳፍጥም እንደ አባቶቹ አንቀላፋ። በዳዊትም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ። በእርሱም ፋንታ ልጁ ኢዮራም ነገሠ።