Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 17:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እስ​ራ​ኤ​ልም ከዳ​ዊት ቤት ተለዩ፤ የና​ባ​ጥ​ንም ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን አነ​ገሡ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል እስ​ራ​ኤ​ልን መለሰ፤ ታላ​ቅም ኀጢ​አት አሠ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እስራኤልን ከዳዊት ቤት ከለየ በኋላ፣ እነርሱ የናባጥን ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እስራኤል እግዚአብሔርን እንዳይከተል በማሳት ትልቅ ኀጢአት እንዲሠራ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከይሁዳ ከለየ በኋላ እስራኤላውያን የናባጥን ልጅ ኢዮርብዓምን መርጠው አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን እንዲተው በማድረግ አሠቃቂ ወደ ሆነ ኃጢአት መራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከይሁዳ ከለየ በኋላ እስራኤላውያን የናባጥን ልጅ ኢዮርብዓምን መርጠው አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን እንዲተዉ በማድረግ አሠቃቂ ወደ ሆነ ኃጢአት መራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እስራኤልንም ከዳዊት ቤት ለየ፤ የናባጥንም ልጅ ኢዮርብዓምን አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን ከመከተል እስራኤልን መለሰ፤ ታላቅም ኀጢአት አሠራቸው።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 17:21
19 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን አለው፥ “ይህን ሠር​ተ​ሃ​ልና፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሕጌን አል​ጠ​ብ​ቅ​ህ​ምና መን​ግ​ሥ​ት​ህን ከአ​ንተ ከፍዬ ለባ​ሪ​ያህ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።


ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንም አለው፥ “ዐሥር ቅዳጅ ውሰድ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ፥ ከሰ​ሎ​ሞን እጅ መን​ግ​ሥ​ቱን እለ​ያ​ታ​ለሁ፤ ዐሥ​ሩ​ንም ነገ​ዶች እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


ስለ በደ​ለ​ውና እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት እስ​ራ​ኤ​ልን ይጥ​ላል።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኤፍ​ሬም ከይ​ሁዳ ከተ​ለ​የ​በት ቀን ጀምሮ ያል​መ​ጣ​ውን ዘመን በአ​ን​ተና በሕ​ዝ​ብህ በአ​ባ​ት​ህም ቤት ላይ ያመ​ጣል፤ እር​ሱም የአ​ሦር ንጉሥ መም​ጣት ነው።”


እኔ ግን በየ​ዋ​ህ​ነቴ እኖ​ራ​ለሁ፤ አቤቱ፦ አድ​ነኝ ይቅ​ርም በለኝ።


እርሱ ግን ለኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች፥ ከንቱ ለሆኑ ጣዖ​ታ​ቱም፥ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ለሠ​ራ​ቸው እን​ቦ​ሶ​ችም ካህ​ና​ትን አቆመ።


ምሽ​ጎ​ቹ​ንም አጠ​ነ​ከረ፤ አለ​ቆ​ች​ንም አኖ​ረ​ባ​ቸው፤ ምግ​ቡ​ንም፥ ዘይ​ቱ​ንም፥ የወ​ይን ጠጁ​ንም አከ​ማ​ቸ​ባ​ቸው።


ከዳ​ዊ​ትም ቤት፤ መን​ግ​ሥ​ቱን ከፍዬ ሰጥ​ቼህ ነበር፤ ነገር ግን በፍ​ጹም ልቡ እንደ ተከ​ተ​ለኝ፥ በፊ​ቴም ቅን ነገር ብቻ እን​ዳ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም እንደ ጠበቀ እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ዳዊት አል​ሆ​ን​ህም።


ልጆቼ ሆይ፥ ይህ አይ​ሆ​ንም፤ እኔ የም​ሰ​ማው ይህ ነገር መል​ካም አይ​ደ​ለ​ምና እን​ዲህ አታ​ድ​ርጉ። ሕዝ​ቡ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከማ​ገ​ል​ገል አት​ከ​ል​ክ​ሉ​አ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን ይንቁ ነበ​ርና የዔሊ ልጆች ኀጢ​አት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበ​ረች።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው።


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምንስ ክፉ ሠራ​ሁ​ብህ? በእ​ኔና በመ​ን​ግ​ሥቴ ላይ ትልቅ ኀጢ​አት አው​ር​ደ​ሃ​ልና፤ ማንም የማ​ያ​ደ​ር​ገው የማ​ይ​ገባ ሥራ በእኔ ሠራ​ህ​ብኝ።”


ይህም ነገር ከገጸ ምድር ለመ​ፍ​ረ​ስና ለመ​ጥ​ፋት በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ላይ ኀጢ​አት ሆነ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ሄዱ፤


ነገር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያሳ​ታ​ቸ​ውን የና​ባ​ጥን ልጅ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ኀጢ​አት ተከ​ተለ፤ እር​ሱ​ንም አል​ተ​ወም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios