1 ቆሮንቶስ 15:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኑ በኤፌሶን ከአውሬ ጋር የታገልሁ ለሰው ብዬ ነውን? ምንስ ይጠቅመኛል? ሙታን የማይነሡ ከሆነ እንግዲህ እንብላ እንጠጣ፥ ነገም እንሞታለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኤፌሶን ከአራዊት ጋራ የታገልሁት ለሰብኣዊ ተስፋ ብቻ ከሆነ ትርፌ ምንድን ነው? ሙታን የማይነሡ ከሆነ፣ “ነገ ስለምንሞት፣ እንብላ፤ እንጠጣ፤” እንደሚሉት መሆናችን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ሰው አስተሳሰብ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ምን ሊፈይድልኝ ነው? ሙታን የማይነሡ ከሆነ፤ ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ሰው አስተሳሰብ እኔ በኤፌሶን ከአራዊት ጋር መታገሌ ጥቅሜ ምንድን ነው? ሙታን ከሞት የማይነሡ ከሆነማ “ነገ ስለምንሞት ኑ እንብላ፤ እንጠጣ” እንደ ተባለው መሆኑ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር ከታገልሁ፥ ሙታንስ የማይነሡ ከሆነ፥ ምን ይጠቅመኛል? ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ። |
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
ለሰው ከመብላትና ከመጠጣት በድካሙም ለሰውነቱ መልካም ነገር ከሚያሳያት በቀር በጎ ነገር የለም፤ ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር እጅ እንደ ተሰጠ አየሁ።
እነሆም፥ በዓልን፥ ደስታንና ሐሴትን አደረጋችሁ፤ በሬዎችንና በጎችንም አረዳችሁ፤ “ነገ እንሞታለን፤ እንብላ፤ እንጠጣም፤” እያላችሁ ሥጋን በላችሁ፤ ወይንንም ጠጣችሁ።
ኑ፤ የወይን ጠጅ እንውሰድ፤ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፤ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል ይላሉ።
ሰውነቴንም እንዲህ እላታለሁ፦ ሰውነቴ ሆይ፥ የሰበሰብሁልሽ ለብዙ ዓመታት የሚበቃሽ የደለበ ብዙ ሀብት አለሽ፤ እንግዲህ ወዲህ ዕረፊ፥ ብዪ፤ ጠጪም፤ ደስም ይበልሽ።
ከዚህም በኋላ በሚሸኙት ጊዜ፥ “እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንደገና እመለሳለሁ፤ አሁን ግን የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም ላደርግ እወዳለሁ” አላቸው፤ ከኤፌሶንም በመርከብ ሄደ።
በእኔ ኀጢአት የእግዚአብሔር ጽድቅ ከጸና እንግዲህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር በሰው ላይ ቅጣትን ቢያመጣ ይበድላልን? አይበድልም፤ የምናገረውንም በሰው ልማድ እናገራለሁ።
ስለ ሰውነታችሁ ድካም በሰው ልማድ እነግራችኋለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰውነታችሁን ለኀጢአትና ለርኵሰት፥ ለዐመፃም እንደ አስገዛችሁ፥ እንዲሁ አሁንም ሰውነታችሁን ለጽድቅና ለቅድስና አስገዙ።
እነዚህ ግን ለመጠመድና ለመጥፋት በፍጥረታቸው እንደ ተወለዱ አእምሮ እንደ ሌላቸው እንስሶች ሆነው፥ በማያውቁት ነገር እየተሳደቡ በጥፋታቸው ይጠፋሉ፤