Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ገላትያ 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ሰውም እን​ኳን የጸ​ና​ውን ኪዳን አይ​ን​ቅም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ት​ምም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ወንድሞች ሆይ፤ ከሰው ዕለታዊ ሕይወት የተለመደውን ምሳሌ አድርጌ ላቅርብ፤ የሰው ኪዳን እንኳ አንድ ጊዜ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሊሽረው ወይም በርሱ ላይ ሊጨምርበት እንደማይችል ሁሉ፣ በዚህም ጕዳይ ቢሆን እንደዚሁ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወንድሞች ሆይ! እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የጸና ኪዳን፥ የሰው ስንኳ ቢሆን፥ ማንም አያፈርሰውም ወይም አይጨምርበትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ወንድሞቼ ሆይ! እስቲ ይህን ነገር በሰው ዘንድ ከተለመደ ነገር ጋር አነጻጽሩት፤ አንድ ሰው የገባው ቃል ኪዳን እንኳ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሰው ሊሽረው ወይም ሊጨምርበት አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እላለሁ። የሰው ስንኳ ቢሆን እርግጠኛውን ኪዳን ማንም አይንቅም ወይም አይጨምርበትም።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 3:15
10 Referencias Cruzadas  

ለአ​ብ​ር​ሃም ያደ​ረ​ገ​ውን፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም የማ​ለ​ውን፤


ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮስ ተነ​ሣና በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቆመ፤ መቶ ሃያ ያህል ሰዎ​ችም በዚያ ሳሉ እን​ዲህ አላ​ቸው።


ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ በሌ​ሎች አሕ​ዛብ እንደ ሆነ በእ​ና​ን​ተም ዋጋ​ዬን አገኝ ዘንድ ሁል​ጊዜ ወደ እና​ንተ ልመጣ እንደ ወደ​ድሁ፥ እስከ ዛሬ ድረ​ስም እንደ ተሳ​ነኝ ልታ​ውቁ እወ​ድ​ዳ​ለሁ።


በእኔ ኀጢ​አት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድቅ ከጸና እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰው ላይ ቅጣ​ትን ቢያ​መጣ ይበ​ድ​ላ​ልን? አይ​በ​ድ​ልም፤ የም​ና​ገ​ረ​ው​ንም በሰው ልማድ እና​ገ​ራ​ለሁ።


ስለ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ድካም በሰው ልማድ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ዕወቁ፤ ቀድሞ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለኀ​ጢ​አ​ትና ለር​ኵ​ሰት፥ ለዐ​መ​ፃም እንደ አስ​ገ​ዛ​ችሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለጽ​ድ​ቅና ለቅ​ድ​ስና አስ​ገዙ።


በውኑ በኤ​ፌ​ሶን ከአ​ውሬ ጋር የታ​ገ​ልሁ ለሰው ብዬ ነውን? ምንስ ይጠ​ቅ​መ​ኛል? ሙታን የማ​ይ​ነሡ ከሆነ እን​ግ​ዲህ እን​ብላ እን​ጠጣ፥ ነገም እን​ሞ​ታ​ለን።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን። በሮሜ ተጽፋ በቲቶ እጅ ወደ ገላ​ትያ ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን፤ አሜን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ር​ሃም ተስ​ፋ​ዉን በሰ​ጠው ጊዜ ይም​ል​በት ዘንድ ከእ​ርሱ የሚ​በ​ልጥ ሌላ ባይ​ኖር፥ በራሱ ማለ።


ሰው ግን ከእ​ርሱ በሚ​በ​ል​ጠው ይም​ላል፤ የክ​ር​ክ​ርም መነ​ሻው በመ​ሐላ ይፈ​ጸ​ማል።


የሙ​አች ሰው ኑዛዜ የጸ​ናች ናት፤ ተና​ዛዡ በሕ​ይ​ወት ባለ​በት ጊዜ አት​ጠ​ቅ​ም​ምና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos