1 ቆሮንቶስ 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽድቅን በመሥራት ደስ ያሰኛል እንጂ፥ ግፍን በመሥራት ደስ አያሰኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍቅር ያለው ሰው እውነት በሆነ ነገር ይደሰታል እንጂ ትክክል ባልሆነ ነገር አይደሰትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ |
ዮቶርም እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ እንደ አዳናቸው ሰምቶ በሁሉ አደነቀ።
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
በእኔ ላይ የተሰበሰቡና የከበቡኝን የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፤ መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እንነሣለን” ይላሉ።
ይህን እንዲህ ላደረገ ሞት እንደሚገባው እነርሱ ራሳቸው የእግዚአብሔርን ፍርድ እያወቁ፥ እነርሱ ብቻ የሚያደርጉት አይደለም፤ ነገር ግን ሌላውን ያነሣሡታል፤ ያሠሩታልም።
ነገር ግን ምን አለ? በየምክንያቱ በእውነትም ቢሆን፥ በሐሰትም ቢሆን፥ ስለ ክርስቶስ ይናገራሉ፤ ሰውንም ሁሉ ወደ እርሱ ይጠራሉ፤ በዚህም ደስ ብሎኛል፤ ወደፊትም ደስ ይለኛል።
ዘወትር እንደምነግራችሁ፥ ልዩ አካሄድ የሚሄዱ ብዙዎች አሉና፤ አሁንም እነርሱ የክርስቶስ የመስቀሉ ጠላቶች እንደ ሆኑ በግልጥ እያለቀስሁ እነግራችኋለሁ።