Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 18:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ዮቶ​ርም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ቸር​ነት ሁሉ፥ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅና ከፈ​ር​ዖን እጅ እንደ አዳ​ና​ቸው ሰምቶ በሁሉ አደ​ነቀ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ዮቶርም እግዚአብሔር እነርሱን ከግብጻውያን እጅ በመታደግ ለእስራኤል ያደረገውን በጎ ነገር ሁሉ በመስማቱ ተደሰተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ይትሮም ጌታ ለእስራኤል ስላደረገው መልካም ነገር ሁሉ፥ ከግብጽም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የትሮም ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ እግዚአብሔር ከግብጻውያን እጅ እስራኤልን ለማዳን ስላደረጋቸው መልካም ነገሮች ደስ ተሰኘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ዮቶርም እግዚአብሔር ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያንም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 18:9
8 Referencias Cruzadas  

መተ​ላ​ለ​ፍ​ህን እንደ ደመና፥ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም እንደ ጭጋግ ደም​ስ​ሼ​አ​ለሁ፤ ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና ወደ እኔ ተመ​ለስ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምሕ​ረ​ትን አድ​ር​ጎ​አ​ልና ሰማ​ያት ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዕ​ቆ​ብን ተቤ​ዥ​ቶ​አ​ልና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ይከ​በ​ራ​ልና የም​ድር መሠ​ረ​ቶች መለ​ከ​ትን ይንፉ፤ ተራ​ሮ​ችና ኮረ​ብ​ቶች በው​ስ​ጣ​ቸው ያሉ ዛፎች ሁሉ፥ እልል ይበሉ።


በስ​ጦ​ታው ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቸር​ነ​ትና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ጋና ዐሰ​ብሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች እው​ነ​ተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸር​ነ​ቱና እንደ ጽድቁ ብዛ​ትም ይቅ​ር​ታ​ውን ያመ​ጣ​ል​ናል።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ ደስ ይበ​ልሽ፤ እር​ስ​ዋ​ንም የም​ት​ወ​ድ​ዱ​አት ሁሉ፥ በአ​ን​ድ​ነት ሐሤት አድ​ርጉ፤ ስለ እር​ስ​ዋም ያለ​ቀ​ሳ​ችሁ ሁሉ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤


እርስ በር​ሳ​ችሁ በወ​ን​ድ​ማ​ማ​ች​ነት መዋ​ደድ ተዋ​ደዱ፤ የም​ት​ራ​ሩም ሁኑ፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ተከ​ባ​በሩ፤ መም​ህ​ሮ​ቻ​ች​ሁ​ንም አክ​ብሩ።


ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ።


አንዱ የአ​ካል ክፍል ቢታ​መም ከእ​ርሱ ጋር የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ይታ​መ​ማሉ፤ አንዱ የአ​ካል ክፍል ደስ ቢለ​ውም የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ሳኦ​ልም ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና” አላ​ቸው። ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ወጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos