ለያዕቆብም፥ “እነሆ፥ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል” ብለው ነገሩት፤ እስራኤልም ተጠነካከረ፤ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ።
1 ዜና መዋዕል 28:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ዳዊት በጉባኤው መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፥ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የዕረፍት ቤት ለመሥራት አሳብ በልቤ መጣብኝ፤ ለዚህም ሥራ የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሥ ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞቼና ወገኖቼ ሆይ፤ ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦት ማደሪያና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን ቤት ለመሥራት ዐስቤ ዕቅድ አውጥቼ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ዳዊት ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ! ስሙኝ፤ ለጌታ ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን የማረፍያ ቤት ለመሥራት እኔ በልቤ አስቤያለሁ፤ ለግንባታም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም በተሰበሰቡ ጊዜ ዳዊት ተነሥቶ፥ እንዲህ አለ፦ “ወገኖቼ ሆይ፥ አድምጡኝ፤ ለአምላካችን የእግር ማሳረፊያ ይሆን ዘንድ የተቀደሰው ታቦት የሚያርፍበት ቤት ለመሥራት ፈልጌ ነበር፤ ለቤተ መቅደሱም ሕንጻ ማሠሪያ የሚሆነውን ዕቃ ሁሉ አዘጋጅቼአለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ አለ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ! ስሙኝ፤ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የዕረፍት ቤት ለመሥራት እኔ በልቤ አስቤያለሁ፤ ለሥራም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤ |
ለያዕቆብም፥ “እነሆ፥ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል” ብለው ነገሩት፤ እስራኤልም ተጠነካከረ፤ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ።
የንጉሡም አገልጋዮች ገብተው፦ ‘እግዚአብሔር የሰሎሞንን ስም ከስምህ ይልቅ መልካም ያድርግ፤ ዙፋኑንም ከዙፋንህ የበለጠ ያድርግ’ ብለው ጌታቸውን ንጉሡ ዳዊትን መረቁ፤” ንጉሡም በአልጋው ላይ ሆኖ ሰገደ።
“እግዚአብሔር ከእግሩ በታች እስኪጥልለት ድረስ በዙሪያው ስለ ነበረ ጦርነት አባቴ ዳዊት ለአምላኩ ለእግዚአብሔር ስም ቤት መሥራት እንዳልቻለ አንተ ታውቃለህ።
“ሂድ፥ ለአገልጋዬ ለዳዊት ንገረው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውስጡ እኖርበት ዘንድ ቤትን የምትሠራልኝ አንተ አይደለህም፤
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጅቻለሁ፤ ደግሞም የማይቈጠር ብዙ የዝግባ እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጅቻለሁ፤ አንተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።
ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው?
አሌፍ። እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት የጽዮንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠቈራት! የእስራኤልን ክብር ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።
እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ መረገጫ ይህ ነው። ዳግመኛም የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው በአለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበት ቦታስ ምን ዐይነት ቦታ ነው?
ከወንድሞችህ መካከል አምላክህ እግዚአብሔር የመረጠውን ለአንተ አለቃ ትሾማለህ፤ ወንድምህ ያልሆነውን ሌላ ሰው በአንተ ላይ መሾም አትችልም።
ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኰራ፥ የአምላኩ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዳይተው፥ ቀኝና ግራም እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ።