Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 22:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አሁ​ንም፥ እነሆ፥ በድ​ህ​ነቴ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መቶ ሺህ መክ​ሊት ወር​ቅና አንድ ሚሊ​ዮን መክ​ሊት ብር፥ ሚዛ​ንም የሌ​ላ​ቸው ብዙ ናስና ብረት አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ ደግ​ሞም የማ​ይ​ቈ​ጠር ብዙ የዝ​ግባ እን​ጨ​ትና ድን​ጋ​ዮች አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤ አን​ተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺሕ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጀት በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለጌታ ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ በሚዛንም የማይመዘን ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፥ አንተም በዚያ ላይ ጨምርበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለ ቤተ መቅደሱ ሥራ የሆነ እንደሆን፥ በበኩሌ ለሕንጻ ሥራ የሚውል ሦስት ሺህ አራት መቶ ቶን ወርቅና ከሠላሳ አራት ሺህ ቶን በላይ የሚሆን ብር አከማችቼልሃለሁ፤ በተጨማሪም ስፍር ቊጥር የሌለው ነሐስና ብረት አዘጋጅቼልሃለሁ፤ እንዲሁም እንጨትና ድንጋይ አዘጋጅቼልሃለሁ፤ ይሁን እንጂ አንተም በተጨማሪ ማግኘት አለብህ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አሁንም፥ እነሆ በምችለው ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጀሁ፤ ደግሞም እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጀሁ፤ አንተም ከዚያ በላይ ጨምር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 22:14
10 Referencias Cruzadas  

በየ​ዓ​መቱ ለሰ​ሎ​ሞን የሚ​መ​ጣ​ለት የወ​ርቅ ሚዛን ስድ​ስት መቶ ስድሳ ስድ​ስት መክ​ሊት ወርቅ ነበረ።


ይህ ሁሉ ሥራ ለተ​ሠ​ራ​በት ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም፤ የና​ሱም ሚዛን ብዙ ነበ​ርና አይ​ቈ​ጠ​ርም ነበር።


ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዓም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ መቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹ​ንም ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚ​ህም ዕቃ​ዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አል​ነ​በ​ረ​ውም።


አን​ተም ብዙ ሠራ​ተ​ኞ​ችን፥ ድን​ጋ​ይና እን​ጨት ወቃ​ሪ​ዎ​ች​ንና ጠራ​ቢ​ዎ​ችን፥ ሥራ​ው​ንም ሁሉ ለማ​ድ​ረግ ጠቢ​ባን ሰዎ​ችን አብ​ዝ​ተህ ጨምር።


ዳዊ​ትም ለበ​ሮቹ ሳንቃ ለሚ​ሆኑ ለም​ስ​ማ​ርና ለመ​ጠ​ረ​ቂያ ብዙ ብረት፥ ከብ​ዛ​ቱም የተ​ነሣ የማ​ይ​መ​ዘን ናስ አዘ​ጋጀ።


እኔም እንደ ጉል​በቴ ሁሉ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወር​ቅን፥ ብርን፥ ናስን፥ ብረ​ትን፥ እን​ጨ​ትን፥ ደግ​ሞም መረ​ግ​ድ​ንና በፈ​ርጥ የሚ​ገባ ድን​ጋ​ይን፥ የሚ​ለ​ጠፍ ድን​ጋ​ይን፥ ልዩ ልዩ መልክ ያለ​ው​ንም ድን​ጋይ፥ የከ​በ​ረ​ው​ንም ድን​ጋይ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ብዙም እብነ በረድ አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ።


ንጉሡ ሰሎ​ሞን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ያሠ​ራ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ዐም​ዶች፥ አን​ዱ​ንም ኵሬ፥ ከመ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም በታች የነ​በ​ሩ​ትን ዐሥራ ሁለ​ቱን የናስ በሬ​ዎች ወሰደ፤ ለእ​ነ​ዚህ የናስ ዕቃ​ዎች ሁሉ ሚዛን አል​ነ​በ​ራ​ቸ​ውም።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የብር ወጭት መቶ ሠላሳ ሰቅል፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ድስት ሰባ ሰቅል ነበረ፤ የዚ​ህም ዕቃ ሁሉ ብር በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።


በብዙ መከራ ከመ​ፈ​ተ​ና​ቸው የተ​ነሣ ደስ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፤ በድ​ህ​ነ​ታ​ቸው ጥል​ቅ​ነ​ትም የለ​ጋ​ስ​ነ​ታ​ቸው ባለ​ጠ​ግ​ነት በዝ​ታ​ለ​ችና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos