Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 7:49 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

49 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ ምን ዐይ​ነት ቤት ትሠ​ሩ​ል​ኛ​ላ​ችሁ? የማ​ር​ፍ​በት ቦታስ ምን ዐይ​ነት ቦታ ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

49 “ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ ማረፊያ የሚሆነኝ ቦታ የት ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

49 ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው? ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 7:49
13 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድ​ርም የእ​ግሬ መረ​ገጫ ናት፤ የም​ት​ሠ​ሩ​ልኝ ቤት ምን ዓይ​ነት ነው? የማ​ር​ፍ​በ​ትስ ስፍራ ምን​ድን ነው?


“ምላ​ሳ​ች​ንን እና​በ​ረ​ታ​ለን፤ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን የእኛ ናቸው፥ ጌታ​ችን ማን ነው?” የሚ​ሉ​ትን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብቻ ለአብ የማ​ይ​ሰ​ግ​ዱ​በት ሰዓት እን​ደ​ም​ት​መጣ እመ​ኝኝ።


ሰው በስ​ውር ቦታ ቢሸ​ሸግ፥ እኔ አላ​የ​ው​ምን? ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንስ የሞ​ላሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሰ​ማ​ሁት እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው ቆመው አየሁ።


እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።


እርሱ ግን መልሶ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፥ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፤” አላቸው።


በሰማይም የሚምለው በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል።


ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ ሰማይ ከሰ​ማ​ያ​ትም በላይ ያለው ሰማይ ይይ​ዝህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ይል​ቁ​ንስ እኔ ለስ​ምህ የሠ​ራ​ሁት ቤት እን​ዴት ያንስ!


“በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው ጋር በም​ድር ላይ ይኖ​ራ​ልን? እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማ​ያ​ትም ይወ​ስ​ንህ ዘንድ አይ​ች​ልም፤ እን​ግ​ዲ​ያስ እኔ የሠ​ራ​ሁት ይህ ቤት ምን​ድን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios