Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 22:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዳዊ​ትም ሰሎ​ሞ​ንን እን​ዲህ አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፤ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ለመሥራት በልቤ ዐስብ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ሆይ! እኔ ለአምላኬ ለጌታ ቤት እንድሠራ በልቤ አስቤ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እንዲህም አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ክብር ቤተ መቅደስ ለመሥራት በልቤ አስቤ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለ “ልጄ ሆይ! እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ቤት እሠራ ዘንድ በልቤ አስቤ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 22:7
16 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ንጉሡ በቤቱ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዙ​ሪ​ያው ያሉ ጠላ​ቶ​ቹን ሁሉ ባወ​ረ​ሰው ጊዜ፥


ባሪ​ያህ ወደ​ዚህ ስፍራ የሚ​ጸ​ል​የ​ውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ፦ በዚያ ስሜ ይሆ​ናል ወዳ​ል​ኸው ስፍራ ወደ​ዚህ ቤት ዐይ​ኖ​ችህ ሌሊ​ትና ቀን የተ​ገ​ለጡ ይሁኑ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “በፊቴ የጸ​ለ​ይ​ኸ​ውን ጸሎ​ት​ህ​ንና ልመ​ና​ህን ሰም​ቻ​ለሁ፤ እንደ ጸሎ​ት​ህም ሁሉ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠ​ራ​ኸ​ውን ቤት ቀድ​ሻ​ለሁ፤ ዐይ​ኖ​ችና ልቤም በዘ​መኑ ሁሉ በዚያ ይሆ​ናሉ።


አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ልጉ ዘንድ ልባ​ች​ሁ​ንና ነፍ​ሳ​ች​ሁን ስጡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ወደ​ሚ​ሠ​ራው ቤት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦ​ትና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ንዋየ ቅድ​ሳት ታመጡ ዘንድ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ የአ​ም​ላ​ክን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መቅ​ደስ ሥሩ።”


ከዚ​ህም በላይ ደግሞ የአ​ም​ላ​ኬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ስለ ወደ​ድሁ፥ ለመ​ቅ​ደሱ ከሰ​በ​ሰ​ብ​ሁት ሁሉ ሌላ የግል ገን​ዘቤ የሚ​ሆን ወር​ቅና ብር አለ​ኝና እነሆ፥ ለአ​ም​ላኬ ቤት ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።


እነሆ፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ታዘ​ዘው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የጣ​ፋ​ጩን ሽቱ ዕጣን ለማ​ጠን፥ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት ለማ​ኖር፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በጥ​ዋ​ትና በማታ፥ በሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በመ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት ለማ​ቅ​ረብ እኔ ልጁ ለአ​ም​ላኬ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ቤት እሠ​ራ​ለሁ፤ እር​ሱ​ንም እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።


ስሙ በዚያ የሚ​ኖር አም​ላክ ይህን ይለ​ውጡ ዘንድ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ው​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ያፈ​ር​ሱት ዘንድ እጃ​ቸ​ውን የሚ​ዘ​ረ​ጉ​ትን ነገ​ሥ​ታ​ትና አሕ​ዛብ ሁሉ ያጥፋ። እኔ ዳር​ዮስ ይህን አዝ​ዣ​ለሁ፤ በት​ጋት ይፈ​ጸም።”


በዚ​ያን ጊዜ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ​ዚያ ወደ መረ​ጠው ስፍራ፥ እኔ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን፥ ቍር​ባ​ና​ች​ሁ​ንም፥ ዐሥ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ ከእ​ጃ​ችሁ ሥራ ቀዳ​ም​ያ​ቱን የተ​መ​ረ​ጠ​ው​ንም መባ​ች​ሁን ሁሉ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም የተ​ሳ​ላ​ች​ሁ​ትን ሁሉ ውሰዱ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠው ስፍራ ከአ​ንተ ሩቅ ቢሆ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጠህ ከላ​ምና ከበግ መን​ጋህ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ እረድ፤ ሰው​ነ​ት​ህም የወ​ደ​ደ​ች​ውን በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ብላው።


ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos