ሶፎንያስ 1:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ፍርድ ቀን ስለ ቀረበ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመሥዋዕት እንደሚታረድ እንስሳ አሳልፎ ለመስጠት እየተዘጋጀ ነው፤ ይሁዳን የሚበዘብዙ ጠላቶችንም ለይቶ አዘጋጅቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታ እግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና። እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውንም ቀድሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ! የጌታ ቀን ቀርቧልና፤ ጌታ መሥዋዕትን አዘጋጅቷል የጠራቸውንም ቀድሶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ። |
ከዚያ በኋላ ግን እኔ እግዚአብሔር “የእግዚአብሔር መሠዊያ” ተብላ የምትጠራውን የእስራኤል ከተማ አስጨንቃለሁ፤ እዚያም ሐዘንና የለቅሶ ዋይታ ይሆናል፤ ከተማይቱም በደም እንደ ተሸፈነ መሠዊያ ትሆናለች።
ለመሥዋዕት የቀረቡ የበግና የፍየል ጠቦቶች በሚሠዉበት ጊዜ ደማቸውና ስባቸው ሰይፉን እንደሚሸፍን የእርሱም ሰይፍ በኤዶማውያን ደምና ስብ ይሸፈናል፤ እግዚአብሔር ይህን መሥዋዕት በቦጽራ ከተማ፥ ይህንንም ታላቅ ዕርድ በኤዶም ምድር ያቀርባል።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
ይህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመረጠው ቀን ነው፤ እርሱ ዛሬ የበቀል እርምጃ ይወስዳል፤ ጠላቶቹንም ይቀጣል። የእርሱም ሰይፍ ብዙዎችን ይበላል፤ በደማቸውም ይለወሳል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙ ምርኮኞቹን መሥዋዕት ያደርጋቸዋል።
በምድሪቱ የምትኖሩ ሕዝብ ሁሉ የመጥፊያችሁ ጊዜ ደርሶአል፤ ጊዜው ደርሶአል፤ ቀኑም ቀርቦአል፤ እርሱም የሁከት ቀን ነው እንጂ በከፍተኛ ቦታዎች የመፈንጠዣ ቀን አይደለም።
እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?
ከሟቾቹ የአንዱ የቅርብ ዘመድ የሆነና ሥርዓተ ቀብሩን የሚፈጽም ሬሳውን ከቤት አውጥቶ ይወስዳል፤ በዚያን ጊዜ በቤት ውስጥ ያለውን አንድ ሰው ጠርቶ “ከአንተ ጋር የቀረ ሌላ ሰው አለን?” ብሎ ይጠይቀዋል፤ ሰውየውም “ማንም የቀረ የለም!” ብሎ ይመልስለታል፤ ጠያቂውም “የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ስለማይገባን ዝም በል!” ይለዋል።
በቤተ መንግሥት የሚያሰሙት ዘፈን በዚያን ቀን ወደ ለቅሶ ይለወጣል፤ የብዙ ሰው ሬሳ በየቦታው ወድቆ ይገኛል፤ በዝምታም በየስፍራው ይጣላል።”
ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ አመጣጡም እየፈጠነ ነው፤ ያ ቀን እጅግ አስፈሪ ነው፤ በዚያን ቀን የሚሰማው ድምፅ አስከፊ ነው፤ ተዋጊው በከፍተኛ ድምፅ ይጮኻል።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።
“ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንደገና እንዲህ ሲል ላከ፤ ‘ወደ ተጠሩት ሰዎች ሂዱና፦ እነሆ፥ የሠርግ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ፍሪዳዎቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶአል፤ ስለዚህ ወደ ሠርጉ ግብዣ ኑ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው።
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።
እርሱም “አዎ! ለሰላም ነው፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ መጥቻለሁ፤ ራሳችሁን በማንጻት ወደ እኔ ኑ” ሲል መለሰላቸው። እሴይና ልጆቹም ራሳቸውን እንዲያነጹ በመንገር ወደ መሥዋዕቱ እንዲመጡ ጠራቸው።
ይሁን እንጂ ሳኦል በዚያን ቀን ምንም ቃል አልተናገረም፤ ሳኦል ስለ ዳዊት ሲያስብ “ምናልባት አንድ ነገር ገጥሞት ይሆናል፤ ወይም በሕጉ መሠረት በሥርዓት አልነጻም ይሆናል” በማለት ያሰላስል ነበር፤