| ኤርምያስ 46:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ይህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመረጠው ቀን ነው፤ እርሱ ዛሬ የበቀል እርምጃ ይወስዳል፤ ጠላቶቹንም ይቀጣል። የእርሱም ሰይፍ ብዙዎችን ይበላል፤ በደማቸውም ይለወሳል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙ ምርኮኞቹን መሥዋዕት ያደርጋቸዋል።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 ያ ቀን ግን የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን። ሰይፍ እስኪጠግብ ድረስ ይበላል፤ ጥማቱም እስኪረካ ድረስ ደም ይጠጣል። በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሥዋዕት አዘጋጅቷልና።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ያ ቀን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን ነው፤ እርሱም ጠላቶቹን የሚበቀልበት የበቀል ቀን ነው፤ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።Ver Capítulo የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የአምላካችን የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ በልቶ ይጠግባል፤ በደማቸውም ይሰክራል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መሥዋዕት በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ነውና።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ያ ቀን ጠላቶቹን የሚበቀልበት የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፥ ሰይፍ በልቶ ይጠግባል በደማቸውም ይሰክራል፥ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።Ver Capítulo |