Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 2:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የሠራዊት አምላክ ትዕቢተኞችና ኩራተኞች የሚዋረዱበትን ቀን ወስኖአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፣ የተኵራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እብሪተኛውንና ትዕቢተኛውን ሁሉ፤ የተኩራራውን በሙሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን በት​ዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውና በኵ​ራ​ተ​ኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለ​ውም ላይ ይሆ​ናል፤ እነ​ር​ሱም ይዋ​ረ​ዳሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፥ እርሱም ይዋረዳል፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 2:12
42 Referencias Cruzadas  

ትሑቶችን ታድናለህ፤ ትዕቢተኞችን ግን ታዋርዳለህ።


“ሁሉን የሚችል አምላክ ፍርድ የሚሰጥበትን ጊዜ ለምን አይወስንም? የእርሱ ታማኞችስ የፍርዱን ቃል እስከ መቼ ይጠባበቃሉ?


እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።


እግዚአብሔር ሆይ! ለእኔ ብርሃኔ ነህ፤ አንተ አምላኬ ጨለማዬን ታበራለህ።


ክፉዎች ሰዎች የሚጠፉበት ቀን እንደ ተቃረበ ስለሚያውቅ እግዚአብሔር በእነርሱ ይስቃል።


አንተ የዓለም ፈራጅ ነህ፤ ስለዚህ ተነሥ፤ ለትዕቢተኞች የሚገባቸውን ቅጣት ስጣቸው።


እግዚአብሔር ትምክሕተኞችን ሁሉ ይጸየፋል፤ ከቅጣት እንዲያመልጡም አያደርጋቸውም።


ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “በኢየሩሳሌምና በጽዮን ተራራ የማደርገውን ሁሉ ከፈጸምኩ በኋላ ስለ ትምክሕቱና ስለ ትዕቢቱ ሁሉ ብዛት የአሦርንም ንጉሠ ነገሥት ደግሞ እቀጣለሁ።”


እነሆ የሠራዊት አምላክ ከዛፍ እንደ ተቈረጠ ቅርንጫፍ እየሰባበረ ያወርዳቸዋል፤ በእነርሱ መካከል ኩራተኛ የሆነውና እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ የታበየው ይዋረዳል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዓለምን ስለ ክፋቱ፥ ክፉዎችን ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የኲራተኞችን ማን አለብኝነት አዋርዳለሁ፤ የትዕቢተኛውንም ጭካኔ አጠፋለሁ።


ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ጥፋትን የሚያመጣበት ቀን ስለ ተቃረበ “ዋይ! ዋይ!” እያላችሁ አልቅሱ።


እነሆ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቊጣና መዓት የሚፈጸምበት ያ ቀን እጅግ አስፈሪ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርስዋ የሚኖረው ኃጢአተኛ ሕዝብ ስለሚደመሰስ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለች።


ነገር ግን ወደ ሙታን ዓለም፥ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ወርደሃል።


ይህንማ ያቀደው የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱም ይህን ያቀደው ባደረጉት ነገር መታበያቸውን እንዲተዉ ለማድረግና የተከበሩትንም ሰዎች ለማዋረድ ብሎ ነው።


እግዚአብሔር በዚያን ዘመን የሰማይ ኀይላትንና የምድር ገዢዎችን የሚቀጣበት ጊዜ ይመጣል።


ምድሪቱ እጅግ ደርቃ ልምላሜዋ ሁሉ ይጠወልጋል፤ የምድርም ታላላቅ ሰዎች ይደክማሉ።


እርሱ ልዑላንን ያዋርዳል፤ የዚህ ዓለም ገዢዎችንም እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል።


ተራራዎችንና ኰረብቶችን አጠፋለሁ፤ በእነርሱ ላይ የበቀሉትን ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ወደ ደረቅ ምድር እለውጣለሁ፤ ኩሬዎችንም አደርቃለሁ።


ሰው ሁሉ የተዋረደ ጐስቋላ ይሆናል፤ ትዕቢተኛ የነበረውም ሁሉ ይዋረዳል።


የእግዚአብሔርን የምሕረት ዓመትና የአምላካችንን የበቀል ቀን እንዳውጅ፥ የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና፥


የመረጥኳቸው ሕዝቤ በሁሉ አቅጣጫ በጭልፊቶች እንደ ተከበበች ወፍ ሆነዋል፤ ስለዚህ ሌሎችም የዱር አራዊት መጥተው ሥጋቸውን በመብላት እንዲደሰቱ ጥሩአቸው።


“የይሁዳን ኲራትና የኢየሩሳሌምን ታላቅ ትዕቢት የማስወግደው በዚህ ዐይነት ነው፤


ያ ቀን ምንኛ አስጨናቂ ይሆናል! እርሱን የመሰለ ቀን የለም፤ ለያዕቆብ ልጆች ለእስራኤላውያን የመከራ ዘመን ይሆናል፤ ሆኖም እነርሱ ከዚያ ሁሉ ጭንቀት ይድናሉ።”


ይህ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የመረጠው ቀን ነው፤ እርሱ ዛሬ የበቀል እርምጃ ይወስዳል፤ ጠላቶቹንም ይቀጣል። የእርሱም ሰይፍ ብዙዎችን ይበላል፤ በደማቸውም ይለወሳል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ሰሜን የሚገኙ ምርኮኞቹን መሥዋዕት ያደርጋቸዋል።


“ትዕቢተኛይቱ ባቢሎን ሆይ! እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በአንቺ ላይ እነሣለሁ፤ አንቺንም የምቀጣበት ጊዜ ደርሶአል።


በእግዚአብሔር ቀን ጦርነቱን ለመቋቋም ይቻል ዘንድ ወደ ፍርስራሹ አልወጣችሁም፤ ወይም የእስራኤልን ቅጥር አልጠገናችሁም።


“እነሆ፥ እኔ ናቡከደነፆር ለሰማይ ንጉሥ ምስጋና፥ ክብርና ውዳሴ አቀርባለሁ፤ እርሱ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ነው፤ መንገዱም ፍትሓዊ ነው፤ በትዕቢት የሚመሩትንም ሁሉ ማዋረድ ይችላል።”


እናንተ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት የምትጠባበቁ ወዮላችሁ! ያ ቀን የጨለማ እንጂ የብርሃን ቀን ስላይደለ ለምን ያንን ቀን ትጠባበቃላችሁ?


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ በእናንተ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፤ ከዚህም ልታመልጡ ፈጽሞ አትችሉም፤ ያ አሠቃቂ ጊዜ ስለሚሆን በትዕቢት መመላለስ አትችሉም።


በምድራችሁ የሚገኙትን ከተሞች አጠፋለሁ፤ ምሽጎቻችሁንም ሁሉ አፈራርሳለሁ፤


በዚያን ቀን በተመሸጉት ከተሞችና በረጃጅም ግንቦች ላይ የጦርነት መለከትና የማስጠንቀቂያ ድምፅ ይሰማል።


ትዕቢተኞችንና ትምክሕተኞችን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ በእኔ ላይ ስለ ፈጸማችሁት በደል በዚያን ጊዜ አታፍሩበትም፤ ከእንግዲህ ወዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ አትታበዩም።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


“ታላቁና አስፈሪው የእኔ የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት እነሆ፥ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ።


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱንም ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል።”


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ግን ከፍ ይላል።”


በኃጢአት የተሞላው የዚህ ሰው ሥጋ ይፈርስ ዘንድ ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል። ይህንንም የምታደርጉት ጌታ ኢየሱስ ለፍርድ በሚመጣበት ቀን የዚህ ሰው ነፍስ እንድትድን ነው።


የጌታ ቀን የሚመጣው፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ ዐይነት መሆኑን እናንተ ራሳችሁ ደኅና አድርጋችሁ ታውቃላችሁ።


ሆኖም መጽሐፍ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ስለሚል እግዚአብሔር የሚሰጠው ጸጋ ከሁሉም ይበልጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos