መዝሙር 56:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ሰዎች ስለሚያስጨንቁኝና ጠላቶቼም ዘወትር ስለሚያሳድዱኝ ማረኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ የሰዎች መረገጫ ሆኛለሁና ማረኝ፤ ቀኑንም ሙሉ በውጊያ አስጨንቀውኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ ከቅዱሳን ስለ ራቁ ሕዝብ፥ ፍልስጥኤማውያን በጋት በያዙት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይቅር በለኝ፥ አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፤ ኀጢአት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ። |
ጠላቶቻችሁ ሁሉ በእናንተ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉ፤ ያሽሟጥጣሉ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፤ እንዲህ ሲሉም ይጮኻሉ፦ “ደመሰስናቸው! እሰይ ይህ የምንመኘው ቀን ነበር! በመጨረሻም አየነው።”
ጌታ የእስራኤልን መኖሪያ ሁሉ ያለ ምሕረት አጠፋ፤ በቊጣውም የይሁዳን ሕዝብ ምሽግ አፈረሰ፤ መንግሥትዋንና ባለ ሥልጣኖቿን ወደ ምድር ጥሎ አዋረደ።
ነገር ግን የፍልስጥኤም ጦር አዛዦች በአኪሽ ላይ ተቈጥተው እንዲህ አሉት፤ “ይህን ሰው ቀድሞ ወደ ሰጠኸው ከተማ መልሰው፤ ከእኛ ጋር አብሮ እንዲዘምት አታድርግ፤ ጦርነቱ በሚፋፋምበት ወቅት በእኛ ላይ ሊነሣ ይችላል፤ እርሱ ከጌታው ጋር ለመስማማት የእኛን ሰዎች ከመግደል ሌላ ምን አማራጭ ይኖረዋል?