አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤
መዝሙር 51:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ይቅር በለኝ፤ ስለ ታላቁ ምሕረትህም ኃጢአቴን ደምስስልኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ መጠን፣ ምሕረት አድርግልኝ፤ እንደ ርኅራኄህም ብዛት፣ መተላለፌን ደምስስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኰራለህ? ሁልጊዜስ ለምን ትበድላለህ? |
አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤
የቀድሞ አባቶቻችን በግብጽ ምድር እርሱ ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ አላስተዋሉም፤ ብዙዎቹን የቸርነት ሥራዎቹን አላስታወሱም፤ በቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁ።
አንተ የእውነት አምላክ ነህ፤ እባክህን ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ! እኔ በጣም በጭንቀት ላይ ነበርኩ አንተ ግን ነጻ አወጣኸኝ፤ አሁንም ራራልኝና ጸሎቴን ስማ።
ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ከተቀደሰውና ከክቡር መኖሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህ የት አሉ? መልካም ፈቃድህና ርኅራኄህስ የት አለ? እነርሱ ከእኛ ርቀዋል።
ለእኛ ስላደረጋቸው ድርጊቶች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ እንደ መሐሪነቱ ስላሳየው ከፍተኛ በጎ አመለካከት፥ ስለ ተትረፈረፈውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምስጉን ድርጊቶቹን እዘረዝራለሁ።
አምላክ ሆይ! እነርሱ እኔን ለመግደል የሸረቡትን ሤራ ታውቀዋለህ፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ይቅር አትበል፤ ኃጢአታቸውም እንዲሰረይላቸው አታድርግ፤ በፊትህ እንዲሸነፉና በብርቱ ቊጣህ እንዲወድቁ አድርግ።”
አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም።