124 ለእኔ ለአገልጋይህ ፍቅርህን አሳይ፤ ሕጎችህንም አስተምረኝ።
124 ለባሪያህ እንደ ምሕረትህ መጠን አድርግ፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ።
124 ለባርያህ እንደ ምሕረትህ አድርግ፥ ሥርዓትህንም አስተምረኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! አመሰግንሃለሁ፤ የአንተን ሕግ አስተምረኝ።
አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም።
እስራኤል ሆይ! ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነና ሰዎችንም የማዳን ኀይል ያለው ስለ ሆነ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
ወደ እኔ ተመለስ፤ ለሚወዱህ ሁሉ እንደምታደርገውም ምሕረት አድርግልኝ።
አድራጎቴን ሁሉ ተናዘዝኩ፤ አንተም ሰማኸኝ፤ እንግዲህ ሕግህን አስተምረኝ።
በኃጢአታችን መጠን አልቀጣንም፤ በበደላችንም ልክ አልከፈለንም።
እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ግን ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አንተ በመረጥከው ጊዜ ጸሎቴን መልሰህ፥ በዘለዓለማዊው ፍቅርህ ማዳንህን አረጋግጥልኝ።
አምላክ ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ይቅር በለኝ፤ ስለ ታላቁ ምሕረትህም ኃጢአቴን ደምስስልኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! ቸርነት በተሞላበት ፍቅርህ ጸሎቴን ስማ፤ በታላቁ ምሕረትህ ወደ እኔ ተመለስ።
“ቀራጩ ግን በሩቅ ቆመና፥ ቀና ብሎ ወደ ሰማይ ለማየት እንኳ አልደፈረም፤ ነገር ግን በእጁ ደረቱን እየመታ፥ ‘አምላክ ሆይ! እኔን ኃጢአተኛውን ማረኝ!’ ይል ነበር።
እግዚአብሔር ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ወደ እኔ ይድረስ፤ በተስፋ ቃልህም መሠረት አድነኝ።
እኛ በጣም ስለ ተዋረድን በአባቶቻችን ኃጢአት ምክንያት አትቅጣን ፈጥነህም ምሕረት አድርግልን።
የሚያስተምራቸውን ቸር መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ የሚመገቡትን መና፥ የሚጠጡትንም ውሃ ሰጠሃቸው።
ከሚያሤሩባቸው ሰዎች በመኖሪያህ ጥላ ሥር ትደብቃቸዋለህ፤ ከመርዘኛ አንደበትም በከለላህ ትጠብቃቸዋለህ።
ሕግህን እጠብቅ ዘንድ በዘለዓለማዊ ፍቅርህ ሕይወትን ስጠኝ።