Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር ምሕረት አታድርግላቸው፤ የፈረሰውን በመሥራታችን በስድብ አዋርደውናልና በደላቸውን አትርሳ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የፈረሰውን በሚሠሩት ፊት የስድብ ናዳ አውርደዋልና በደላቸውን ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አታጥፋው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጠላቶቻችንም፦ “በመካከላቸው እስክንገባና እስክንገድላቸው ድረስ፥ ሥራቸውንም እስክናስተጓጉል ድረስ አያውቁም፥ አያዩምም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በደ​ላ​ቸ​ው​ንም አት​ክ​ደን፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከፊ​ትህ አይ​ደ​ም​ሰስ፤ በሠ​ራ​ተ​ኞች ፊት አስ​ቈ​ጥ​ተ​ው​ሃ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በደላቸውንም አትክደን፥ ኃጢአታቸውም ከፊትህ አይደምሰስ፥ በሠራተኞች ፊት አስቆጥተውሃልና።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 4:5
14 Referencias Cruzadas  

አምላክ ሆይ! እነርሱ እኔን ለመግደል የሸረቡትን ሤራ ታውቀዋለህ፤ ስለዚህ ክፋታቸውን ይቅር አትበል፤ ኃጢአታቸውም እንዲሰረይላቸው አታድርግ፤ በፊትህ እንዲሸነፉና በብርቱ ቊጣህ እንዲወድቁ አድርግ።”


እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶቹን ኃጢአት ያስብበት፤ የእናቱንም ኃጢአት ይቅር አይበልላት።


የናስ አንጥረኛው እስክንድር ከፍተኛ ጒዳት አደረሰብኝ፤ ጌታ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


በደልህን እንደ ደመና ኃጢአትህን እንደ ማለዳ ጭጋግ አስወግጄአለሁ፤ ስለ አዳንኩህ ወደ እኔ ተመለስ።”


ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።


አምላክ ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ይቅር በለኝ፤ ስለ ታላቁ ምሕረትህም ኃጢአቴን ደምስስልኝ።


ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤ በደሌን ሁሉ ደምስስ።


እኛም ቅጽሩን መልሶ የማነጹን ሥራ ቀጠልን፤ ሕዝቡ በትጋት በመሥራቱ ሥራው እየተፋጠነ ሄዶ ግማሽ ደረሰ።


ከዚህም የተነሣ በሁሉም ላይ ኀፍረትና ውርደት ይደርስባቸዋል፤ ጌታ ሆይ! በደላቸውን ይቅር አትበል!


“ ክፉ ሥራቸውን ሁሉ ተመልከት፤ በበደሎቼ ሁሉ ምክንያት በእኔ ላይ እንዳደረግኸው በእነርሱም ላይ አድርግ ዘወትር ስለምቃትት ልቤ እየደከመብኝ ነው።”


ደክሞት ተስፋ በመቊረጥ ላይ ሳለ ድንገተኛ አደጋ እጥልበታለሁ፤ በዚያን ጊዜ እርሱ ድንጋጤ ላይ ይወድቃል፤ ተከታዮቹም ጥለውት ይሸሻሉ ንጉሡንም ለብቻው አግኝቼ እገድለዋለሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios