በጣም በርትተውብኝ ከነበሩት ከኀይለኞች ጠላቶቼና ከሚጠሉኝ ሰዎች ሁሉ እጅ እግዚአብሔር አዳነኝ።
ከብርቱ ጠላቶቼ አዳነኝ፤ ከሚበረቱብኝ ባላጋሮቼም ታደገኝ።
ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።
እግዚአብሔር ዳዊትን ከሳኦልና ከሌሎቹም ጠላቶቹ እጅ በመታደግ ባዳነው ጊዜ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ክብር ዘመረ፦
እግዚአብሔር ተቈጥቶ ሰውነቴን ቈራረጠ፤ በጥላቻም ጥርሱን አፋጨብኝ፤ ጠላቴም ዐይኑን አፈጠጠብኝ።
እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ሆኖ ስለሚረዳኝ፥ የጠላቶቼን ውድቀት አያለሁ።
መከራ ዙሪያዬን በሚከበኝ ጊዜ መከታ ሆነህ በሕይወት ትጠብቀኛለህ፤ በቊጣ የተነሡብኝ ጠላቶቼን ትቃወማቸዋለህ፤ በኀይልህም ትታደገኛለህ።
በጣም ተስፋ የቈረጥሁ ስለ ሆነ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮኽ ስማኝ፤ እጅግ በርትተውብኛልና ከጠላቶቼ አድነኝ።
እጅህን ከላይ ስደድ፤ ከጥልቅ ውሃ ውስጥ ስበህ አውጣኝ፤ ታደገኝም፤ ከባዕዳን ኀይል አድነኝ።
ጠላቶቼ ምን ያኽል እንደ በዙ እይ፤ ምን ያኽል እንደ ጠሉኝም ተመልከት።
ጌታ ሆይ! ሁለመናዬ እንዲህ ብሎ ይናገራል፤ ተበዳዮችን ከበደለኛ የሚያድን፥ ድኾችንና ተጨቋኞችን ከነጣቂዎች የሚጠብቅ እንደ አንተ ያለ ማነው?
ያለ ምክንያት ጠላት የሆኑብኝ ኀያላን ናቸው፤ በስሕተትም የሚጠሉኝ ብዙዎች ናቸው።
እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትን አድርግልኝ! ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት! ከሞትም አድነኝ።
የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ስለ ነበር፥ ይህ ሰው በእኛ ላይ እንዲነግሥ አንፈልግም ሲሉ እርሱ ከሄደ በኋላ መልእክተኛ ላኩ።