19 ጠላቶቼ ምን ያኽል እንደ በዙ እይ፤ ምን ያኽል እንደ ጠሉኝም ተመልከት።
19 ጠላቶቼ እንዴት እንደ በዙ ተመልከት፤ እንዴት አምርረው እንደሚጠሉኝ እይ።
19 ጠላቶቼ እንደበዙ እይ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
ቀጥሎም ዳዊት ለአቢሳና ለመኳንንቱ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “የራሴ ልጅ ሊገድለኝ ይፈልጋል፤ ታዲያ በዚህ ብንያማዊ ሰው ስለምን ትደነቃላችሁ? እኔን እንዲረግመኝ እግዚአብሔር ነግሮታል፤ ስለዚህ ተዉት፥ የአሰበውን ያድርግ፤
እግዚአብሔር ጻድቃንንና ኃጢአተኞችን ይፈትናል፤ ዐመፅ የሚወዱትን ግን ይጠላቸዋል።
መከራ ዙሪያዬን በሚከበኝ ጊዜ መከታ ሆነህ በሕይወት ትጠብቀኛለህ፤ በቊጣ የተነሡብኝ ጠላቶቼን ትቃወማቸዋለህ፤ በኀይልህም ትታደገኛለህ።
እግዚአብሔር ሆይ! ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ከዐመፀኞች እጅም ጠብቀኝ።
ሌሎችን በሐሰት የሚከስሱ በምድር ላይ ጸንተው አይኑሩ፤ ክፉ ነገር በጨካኞች ሰዎች ላይ ይድረስ፤ ይደምስሳቸውም።
እግዚአብሔር ሆይ! ከክፉዎች ኀይል ጠብቀኝ፤ እኔን ለመጣል ከሚያቅዱ ከዐመፀኞች ሰዎች ጠብቀኝ።
ጠላቴ በማሳደድ ተከታተለኝ፤ በጨለማ ውስጥም አስሮ አጐሳቈለኝ፤ ከብዙ ዘመናት በፊት እንደ ሞቱ ሰዎች ሆኜአለሁ።
ከጠላቶቼም ታድነኛለህ። ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛለህ።
የሐሰት ምስክሮች ዐመፅን እየተናገሩ በእኔ ላይ ስለ ተነሡ ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።
ክፉ ሰዎች ሲያጠቁኝና ሊገድሉኝ ሲቃጡ እነርሱ ራሳቸው ተሰናክለው ይወድቃሉ።
ያለ ምክንያት ጠላት የሆኑብኝ ኀያላን ናቸው፤ በስሕተትም የሚጠሉኝ ብዙዎች ናቸው።
እኔ ደግ ሥራ በመሥራቴ በመልካም ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ፤ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥተዋል።
አንተ ተንኰለኛ ጥፋትህን ታሤራለህ፤ አንደበትህ እንደ ተሳለ ምላጭ ነው።
ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ ያጠቁኛል፤ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ የሚያሳድዱኝ ብዙዎች ናቸው።
ጥርሶቻቸው እንደ ጦሮችና ቀስቶች፥ ምላሶቻቸው እንደ ተሳሉ ሰይፎች በሆኑ፥ ሰውን በሚበሉ አንበሶች መካከል ተደፍቼ ተኝቼአለሁ።
አምላክ ሆይ! ትዕቢተኞች በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤ አንተን የማይፈሩ ጨካኞች ሰዎች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ።
የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሕዝቡን ስለ ፈሩ ኢየሱስን ይዘው የሚገድሉበትን ዘዴ በስውር ይፈልጉ ነበር።
እነርሱ ግን “ይህ ሰው ከገሊላ ጀምሮ እስከዚህ ድረስ፥ በይሁዳ ምድር ሁሉ እያስተማረ ሕዝቡን ለሁከት ያነሣሣል” እያሉ በጥብቅ ከሰሱት።