መዝሙር 150:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመለከት አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ ወድሱት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመለከት ድምፅ አወድሱት፥ በበገናና በመሰንቆ አወድሱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት፤ |
ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ የበገና፥ የመሰንቆ፥ የከበሮ፥ የጸናጽልና የቃጭል ድምፅ እያሰሙ ለእግዚአብሔር ክብር በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።
በዚህ ዐይነት መላው እስራኤላውያን ጥሩምባና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽል እያንሿሹ፥ መሰንቆና በገና እየደረደሩ በሆታና በእልልታ የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
ሄማንና ይዱታን ለእምቢልታዎች፥ ለጸናጽሎችና የምስጋና መዝሙር ሲዘመር ለሚጠቀሙባቸው ሌሎች የዜማ ዕቃዎች ኀላፊዎች ሆኑ፤ የይዱቱን ልጆች አባሎች ለቅጽር በሮች ጥበቃ ኀላፊዎች ሆኑ።
ንጉሥ ዳዊትና የሌዋውያን አለቆች የአሳፍን፥ የሔማንና የይዱቱን ልጆች መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን መዝሙር በመሰንቆ፥ በበገናና በጸናጽል እየታጀቡ እንዲዘምሩ ለዩአቸው። ለዚህ አገልግሎት የተመደቡት ሰዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦
ከእነርሱም ጋር እምቢልታ የሚነፉ አንድ መቶ ኻያ ካህናት ነበሩ፤ እነዚህ መዘምራን ሁሉ በመለከት፥ በጸናጽል፥ በበገናና በሌሎችም የሙዚቃ መሣሪያዎች እየታጀቡ፦ “ቸር ስለ ሆነ፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ” በማለት በአንድ ድምፅ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር። በዚህ ጊዜ በድንገት የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጥ አንጸባራቂ ብርሃን የሞላበት ደመና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ስለ ሞላው ካህናቱ የአምልኮ አገልግሎታቸውን ሊያከናውኑ አልቻሉም።
የመለከት የእንቢልታ የመሰንቆ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንት፥ የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ በምድር ላይ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል እንድትሰግዱ ታዛችኋል።
እንዲሁም በደስታ በዓሎቻችሁ፥ ማለት በወር መጀመሪያና በሌሎችም የተወሰኑ በዓሎቻችሁ፥ በሚቃጠል መሥዋዕትና በአንድነት መሥዋዕታችሁ ላይ መለከቶችን ትነፋላችሁ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ስለ እናንተ አስታዋሾች ይሆናሉ። እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።”