Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 150:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በመ​ለ​ከት ድምፅ አመ​ስ​ግ​ኑት፤ በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ አመ​ስ​ግ​ኑት፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ ወድሱት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በመለከት ድምፅ አወድሱት፥ በበገናና በመሰንቆ አወድሱት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በመለከት አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 150:3
17 Referencias Cruzadas  

ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ በእ​ል​ልታ ቀንደ መለ​ከት እየ​ነፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት አመ​ጡ​አት።


ዳዊ​ትና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ በዜማ መሣ​ሪ​ያ​ዎች በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በከ​በ​ሮና በነ​ጋ​ሪት፥ በጸ​ና​ጽ​ልና በዕ​ን​ዚራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሙሉ ኀይ​ላ​ቸው ይጫ​ወቱ ነበር።


ዘካ​ር​ያስ፥ አዝ​ኤል፥ ሰሚ​ራ​ሞት፥ ኢያ​ሔል፥ ዑኒ፥ ኤል​ያብ፥ መዕ​ሤያ፥ በና​ያስ በመ​ሰ​ንቆ በል​ዑል ቃል ያዜሙ ነበር።


ካህ​ና​ቱም ሰበ​ንያ፥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ፥ ናት​ና​ኤል፥ ዓማ​ሣይ፥ ዘካ​ር​ያስ፥ በና​ያስ፥ አል​ዓ​ዛ​ርም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት መለ​ከት ይነፉ ነበር። አብ​ዲ​ዶ​ምና ኢያ​ኤ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት በረ​ኞች ነበሩ።


እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤል ሁሉ በይ​ባቤ፥ ቀንደ መለ​ከ​ትና እን​ቢ​ልታ እየ​ነፉ፥ ጸና​ጽ​ልና መሰ​ን​ቆም፥ በገ​ናም እየ​መቱ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ካህ​ናቱ ከፍ አድ​ር​ገው ለማ​ሰ​ማት መለ​ከ​ትና ጸና​ጽል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መዝ​ሙ​ራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤ​ዶ​ታም ልጆች ግን በረ​ኞች ነበሩ።


ዳዊ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆ​ችም ከአ​ሳ​ፍና ከኤ​ማን ከኤ​ዶ​ት​ምም ልጆች በመ​ሰ​ን​ቆና በበ​ገና፥ በጸ​ና​ጽ​ልም የሚ​ዘ​ምሩ ሰዎ​ችን ለማ​ገ​ል​ገል ለዩ፤ በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውም ሥራ የሚ​ሠሩ ሰዎች ቍጥር ይህ ነበረ።


በበ​ገ​ናና በመ​ሰ​ንቆ፥ በመ​ለ​ከ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገቡ።


መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ መዘ​ም​ራኑ በአ​ን​ድ​ነት ሆነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” እያሉ በአ​ንድ ቃል ድም​ፃ​ቸ​ውን ወደ ላይ ከፍ አድ​ር​ገው በመ​ለ​ከ​ትና በጸ​ና​ጽል፥ በዜ​ማም ዕቃ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባመ​ሰ​ገኑ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ብሩ ደመና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው።


የዐ​መ​ፀኛ አፍና የኀ​ጢ​አ​ተኛ አፍ በላዬ ተላ​ቅ​ቀ​ዋ​ልና። በሽ​ን​ገላ አን​ደ​በ​ትም በላዬ ተና​ገሩ፤


ስሙን በደ​ስታ ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፥ በከ​በ​ሮና በበ​ገና ይዘ​ም​ሩ​ለ​ታል።


ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትከ​ብ​ራ​ለች፥ ገሮ​ችም ይስሙ፥ ደስም ይበ​ላ​ቸው።


አቤቱ፥ ወን​ዞች ከፍ ከፍ አደ​ረጉ፥ ወን​ዞች ቃሎ​ቻ​ቸ​ውን ከፍ ከፍ አደ​ረጉ።


ደግሞ በደ​ስ​ታ​ችሁ ቀን፥ በበ​ዓ​ላ​ታ​ች​ሁም ዘመን፥ በወ​ርም መባቻ፥ በሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁና በደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ላይ መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ እነ​ር​ሱም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos