Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 149:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በማሸብሸብ ስሙን ያመስግኑት፤ ከበሮ እየመቱና በገና እየደረደሩ ያመስግኑት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስሙን በሽብሸባ ያመስግኑ፤ በከበሮና በመሰንቆ ይዘምሩለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስሙን በደ​ስታ ያመ​ሰ​ግ​ናሉ፥ በከ​በ​ሮና በበ​ገና ይዘ​ም​ሩ​ለ​ታል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 149:3
19 Referencias Cruzadas  

ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ሽርጥ በወገቡ ዙሪያ ታጥቆ እግዚአብሔርን በማክበር በሙሉ ኀይሉ ያሸበሽብ ነበር፤


ታቦቱን ይዘው ወደ ከተማ በሚገቡበት ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ተመለከተች፤ ንጉሡ ዳዊት እየዘለለ ሲያሸበሽብ አይታም በልብዋ ናቀችው፤


ሄማንና ይዱታን ለእምቢልታዎች፥ ለጸናጽሎችና የምስጋና መዝሙር ሲዘመር ለሚጠቀሙባቸው ሌሎች የዜማ ዕቃዎች ኀላፊዎች ሆኑ፤ የይዱቱን ልጆች አባሎች ለቅጽር በሮች ጥበቃ ኀላፊዎች ሆኑ።


ወንዶች ልጆቹ ሁሉ በቤተ መቅደስ የሚካሄደውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት በማጀብ በአባታቸው መሪነት ጸናጽል ያንሿሹና መሰንቆና በገና ይደረድሩ ነበር፤ አሳፍ፥ ይዱታንና ሄማን በንጉሡ ሥልጣን ሥር ነበሩ።


ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም በእምቢልታ፥ በዋሽንትና በበገና ድምፅ እየታጀቡ በሰልፍ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ፤


ንጉሥ ሕዝቅያስ እግዚአብሔር በነቢዩ ጋድና በነቢዩ ናታን አማካይነት ለንጉሥ ዳዊት የሰጠውንና ዳዊትም ተግባራዊ ያደረገውን ትእዛዝ በመከተል በበገና፥ በጸናጽልና በመሰንቆ የሠለጠኑ ሌዋውያንን በቤተ መቅደሱ ውስጥ መደበ፤


ሠራተኞቹ የቤተ መቅደሱን መሠረት ማኖር በጀመሩበት ጊዜ ካህናቱ ልብሰ ተክህኖአቸውን ለብሰው በእጃቸው እምቢልታ በመያዝ የአሳፍ ቤተሰብ ተወላጆች የሆኑ ሌዋውያንም ጸናጽል ይዘው በረድፍ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ከንጉሥ ዳዊት ዘመን ጀምሮ ተያይዞ በመጣው መመሪያ መሠረት በመዝሙር እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


አንተ ሐዘኔን ወደ ደስታ ለወጥክልኝ፤ ትካዜዬን ከእኔ አስወገድክልኝ፤ የማቅ ልብሴን አውልቀህ ደስታን አለበስከኝ።


እግዚአብሔርን በመሰንቆ አመስግኑት፤ ዐሥር አውታር ባለውም በገና ዘምሩለት።


መዝሙር ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚያሰኝ ዜማ አሰሙ።


ለበዓሉ ክብር መለከት ንፉ፤ አዲስ ጨረቃ ስትወጣና ሙሉ ጨረቃ ስትሆን ይህንኑ አድርጉ።


ዘማሪዎችና ጨፋሪዎች “የበረከታችን ሁሉ መገኛ ጽዮን ናት” እያሉ በደስታ ይዘምራሉ።


የአሮን እኅት ነቢይቱ ማርያም ከበሮዋን አነሣች፤ ሌሎችም ሴቶች ከበሮዎቻቸውን እየመቱና እየጨፈሩ ይከተሉአት ጀመር፤


ልጃገረዶቻቸውም በደስታ ይጨፍራሉ፤ ወንዶች ወጣቶችና ሽማግሌዎችም ደስ ይላቸዋል፤ አጽናናቸዋለሁ፤ ለቅሶአቸውን ወደ ደስታ፥ ሐዘናቸውንም ወደ ሐሴት እለውጣለሁ፤


ሕዝቤ እስራኤል ሆይ፥ እንደገና ትገነባላችሁ፤ ትገነቢአለሽም፥ እንደገና ከበሮ ትይዢአለሽ፤ ከሚደሰቱት ጋር አብረሽ በመውጣት ትጨፍሪአለሽ።


ዮፍታሔ በምጽጳ ወዳለው ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሴት ልጁ አታሞ ይዛ እየጨፈረች ልትቀበለው ወጣች፤ ያለ እርስዋም ሌላ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አልነበረውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos