Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 150 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሃሌ ሉያ። ጌታን በመቅደሱ አወድሱት፥ በኃይሉ ጠፈር አወድሱት።

2 ስለ ታላላቅ ሥራዎቹ አወድሱት፥ እንደ ታላቅነቱ ብዛት አወድሱት።

3 በመለከት ድምፅ አወድሱት፥ በበገናና በመሰንቆ አወድሱት።

4 በከበሮና በሽብሸባ አወድሱት፥ በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።

5 ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አወድሱት፥ ድምፁ በሚሰማ ጸናጽል አወድሱት።

6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ ጌታን ያወድስ። ሃሌ ሉያ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos