መዝሙር 150 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ሃሌ ሉያ። 1 እግዚአብሔርን በተቀደሱ ቦታዎች አመስግኑት፤ በኀይሉ ጽናት አመስግኑት። 2 በከሃሊነቱ አመስግኑት፤ እንደ ታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት። 3 በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት፤ 4 በከበሮና በሽብሸባ አመስግኑት፤ አውታር በአለው መሣሪያና በእንዚራ አመስግኑት። 5 ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ በጸናጽልና በእልልታ አመስግኑት። 6 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግነው። ሃሌ ሉያ። |