ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት እግዚአብሔር ኤልያስን “ሄደህ ራስህን ለንጉሥ አክዓብ ግለጥለት፤ እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ” አለው፤
መዝሙር 135:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብ ያዘለ ደመናን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜ መብረቅ እንዲኖር ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቦታው ያወጣዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያስነሣል፤ መብረቅ ከዝናብ ጋራ እንዲወርድ ያደርጋል፤ ነፋሳትንም ከማከማቻው ያወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድር ዳርቻ ደመናትን ያወጣል፥ በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት እግዚአብሔር ኤልያስን “ሄደህ ራስህን ለንጉሥ አክዓብ ግለጥለት፤ እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ” አለው፤
በእርሱ ትእዛዝ ከሰማይ በላይ ያሉ ውሃዎች የመናወጥ ድምፅ ያሰማሉ፤ እርሱ ደመናዎችን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜም መብረቅ እንዲበርቅ ያደርጋል፤ ነፋስንም ከማከማቻው ይልካል።
ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።
በሰማይ ያለው ውሃ በእርሱ ትእዛዝ ይናወጣል፤ እርሱ ደመናትን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ ከዝናብ ጋርም መብረቅ እንዲበርቅ ያደርጋል፤ ከማከማቻው በማውጣት ነፋስ እንዲነፍስ ያደርጋል።
እግዚአብሔር ግን በባሕሩ ላይ ከባድ ነፋስን አስነሣ፤ በባሕሩም ላይ የተቀሰቀሰው ማዕበል ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ መርከቢቱ ልትሰበር ተቃረበች፤
እግዚአብሔር በበልግ ወራት ዝናብ እንዲሰጣችሁ ለምኑት፤ ዝናብ ያዘለ ደመናን የሚልክ እግዚአብሔር ነው፤ ዝናብንና የመስክ አትክልትን ለሁሉም የሚሰጥ እርሱ ነው።
ነፋስ ወደ ፈለገው አቅጣጫ ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ፤ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣና ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው።”