25 ትእዛዝ በሰጠ ጊዜ ዐውሎ ነፋስ ነፈሰ፤ ማዕበሉም ተንቀሳቀሰ።
25 እርሱ ተናግሮ ዐውሎ ነፋስን አስነሣ፤ ነፋሱም ማዕበሉን ከፍ ከፍ አደረገ።
25 ተናገረ፥ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፥ ሞገዶችንም አስነሣ።
እግዚአብሔር ግን በባሕሩ ላይ ከባድ ነፋስን አስነሣ፤ በባሕሩም ላይ የተቀሰቀሰው ማዕበል ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ መርከቢቱ ልትሰበር ተቃረበች፤
ታላቅ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ስለ ተነሣ ማዕበሉ ጀልባይቱን ሊያሰጥማት ደረሰ፤ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር።
እሳትና በረዶ፥ ዐመዳይና ደመና፥ ትእዛዙን የምትፈጽሙም ብርቱዎች ነፋሳት እግዚአብሔርን አመስግኑ።
እርሱ ባዘዘው መሠረት ሊቈጠር የማይችል የአንበጣና የኲብኲባ መንጋ መጣ።
እግዚአብሔር ሆይ! ባሕሮች ይነሣሉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ይጮኻሉ፤ የሞገዳቸውም ድምፅ ይሰማል።
ኀይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለ ነበር፤ ባሕሩ ተናወጠ።
ዝናብ ያዘለ ደመናን ከምድር ዳርቻ ያመጣል፤ በዝናብ ጊዜ መብረቅ እንዲኖር ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቦታው ያወጣዋል።
ተናካሽ ዝንቦችና ተናካሽ ትንኞች በአገሩ ሁሉ ላይ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።
መርከበኞቹም እጅግ ስለ ፈሩ እያንዳንዱ ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱን ክብደት ለመቀነስ አስበው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ እያወጡ ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን በመርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ በመተኛቱ በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር።