እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከል ሰላም ስለ ነበረ ሁለቱም የጋራ ስምምነት ውል አደረጉ።
መዝሙር 127:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ የቤት ሠሪዎች ድካም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ የከተማ ጠባቂዎች ትጋት ከንቱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዕርገት መዝሙር። ጌታ ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፥ ጌታ ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ብፁዓን ናቸው። |
እግዚአብሔር አስቀድሞ የሰጠውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ለሰሎሞን ጥበብን ሰጠው፤ በኪራምና በሰሎሞን መካከል ሰላም ስለ ነበረ ሁለቱም የጋራ ስምምነት ውል አደረጉ።
ንጉሥ ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞንም እንዲህ አለ፤ “አይዞህ በርታ ሥራውንም በቶሎ ጀምር፤ ምንም ነገር አይግታህ፤ እኔ የማገለግለው እግዚአብሔር አምላክ ከአንተ ጋር ነው፤ ለቤተ መቅደሱ ሥራ ያለህን አገልግሎት እስክትፈጽም ድረስ ከአንተ አይለይም፤ አይተውህም፤ ከቶም አይጥልህም፤
አንተ የምታዘውን፥ ትእዛዞችህን ደንቦችህንና ድንጋጌዎችህን ሁሉ እንዲፈጽምና ይህን ሁሉ ዝግጅት ያደረግኹለትን ቤተ መቅደስ እንዲሠራ ለልጄ ለሰሎሞን ከሙሉ ልብ የመነጨ ፈቃደኛነትን ስጠው።”
በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤
“የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ሁሉም ዕውቀት የላቸውም፤ እነርሱም፥ እንደሚያንቀላፉ፥ እንደሚጋደሙ፥ እንደሚያልሙና መጮኽ እንደማይችሉ ውሾች ናቸው።
በባቢሎን ቅጥር ላይ አደጋ ጣሉ የሚል ምልክት አሳዩ! ጥበቃውን አጠናክሩ! ሰላዮችን መድቡ! ደፈጣ ተዋጊዎችንም አዘጋጁ፤ ይህንንም የምታደርጉት እግዚአብሔር በባቢሎን ሕዝብ ላይ ያቀደውንና የተናገረውን ተግባራዊ ስለሚያደርግ ነው።
የእርሱ ከተማ ከዳር እስከ ዳር የተያዘች መሆንዋን ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንዱ ሩዋጭ ለሌላው ሩዋጭ፥ አንዱ መልእክተኛ ለሌላው መልእክተኛ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይሯሯጣሉ።
ባለጸጋ እንድትሆን ኀይልና ብርታት የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ እርሱ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።