ዘኍል 14:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እኔን የሚንቀው እስከ መቼ ነው? ብዙ ተአምራትን በፊቱ አድርጌአለሁ፤ ታዲያ፥ በእኔ መታመንን እምቢ የሚለው እስከ መቼ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? እነዚህን ሁሉ ታምራት በመካከሉ እያደረግሁ የማያምንብኝስ እስከ መቼ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? በመካከላቸውም ስላደረግሁት ተአምራት ሁሉ እንኳ እስከ መቼ ድረስ በእኔ አያምኑም? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስቈጡኛል? በፊታቸውስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምኑብኝም? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? በፊቱስ ባደረግሁት ተአምራት ሁሉ እስከ መቼ አያምንብኝም? |
ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ንጉሡ ሄደው እንዲህ አሉት፤ “የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለእኔ መታዘዝን እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? አሁንም ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤
የሚነግርህን በማዳመጥ ለእርሱ ታዘዝ፤ በእርሱም ላይ አታምፅ፤ ለእርሱ ሙሉ ሥልጣን የሰጠሁት ስለ ሆነ የምትፈጽመውን ዐመፅ እየተመለከተ ይቅርታ አያደርግልህም።
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
እነዚህ በክፋት የተሞሉ ሕዝብ ለእኔ መታዘዝን እምቢ ብለዋል፤ ከምንጊዜውም ይልቅ እልኸኞች ሆነዋል፤ ባዕዳን አማልክትን በማምለክ ያገለግላሉ፤ ከዚህም የተነሣ እነርሱ ዋጋቢስ ሆኖ እንደ ቀረው እንደዚያ መታጠቂያ ይሆናሉ።
ነገር ግን እስራኤላውያን በበረሓ ሳሉ እንኳ በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ለሚታዘዝለት ሁሉ ሕይወትን የሚያስገኝለትን ሕጌንና ሥርዓቴን ጣሱ፤ ፈጽመውም ሰንበትን አረከሱ፤ በዚያም በበረሓ ቊጣዬን በእነርሱ ላይ በመግለጥ ላጠፋቸው አስቤ ነበር፤
የሰማርያ ሕዝብ ሆይ! በጥጃ ምስል የተሠራ ጣዖታችሁን ተጸይፌአለሁ፤ ቊጣዬ በእናንተ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ ከበደል የማትነጹት እስከ መቼ ነው?
ስለዚህ ለቀድሞ አባቶቻቸው ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር በፍጹም አይገቡም፤ እኔን ከናቁኝ ሰዎች መካከል አንድ እንኳ ወደዚያች ምድር ከቶ አይገባም።
“እነዚህ ክፉዎች የሆኑ ሰዎች በእኔ ላይ የሚያጒረመርሙት እስከ መቼ ነው? እነዚህ አጒረምራሚዎች እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቻለሁ።
በዚያን ቀን እግዚአብሔር እጅግ ተቈጥቶ እንዲህ አለ፤ ‘በእኔ በመተማመን ስላልጸኑ፥ ከግብጽ ምድር ከወጡት ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ የሆኑ ሁሉ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ከቶ እንደማይገቡ ምዬአለሁ።’
ኢየሱስም “እናንተ የማታምኑ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!” አላቸው።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታምኑ ሰዎች! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጁን ወደ እኔ አምጡት!”
የአባቴን ሥራ የምሠራ ከሆንኩ ግን በእኔ እንኳ ባታምኑ በሥራዬ እመኑ፤ በዚህ ዐይነት አብ በእኔ እንደ ሆነና እኔም በአብ እንደ ሆንኩ በሚገባ ታውቃላችሁ።”
ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ይህን ሁሉ ካዩ በኋላ እኔንም አባቴንም ጠልተዋል።
ይህም ሆኖ የምትሰፍሩበትን ቦታ ለመፈለግና የምትሄዱበትን መንገድ ለማሳየት ቀን በደመና ሌሊት በእሳት፥ በፊታችሁ በሚሄደው በአምላካችሁ በእግዚአብሔር አልተማመናችሁም።