ነህምያ 12:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋውያኑ በሐሻብያ፥ በሼሬብያ፥ በኢያሱ፥ በቢኑይና በቃድሚኤል መሪነት በሁለት ቡድኖች ተከፈሉ። ሁለቱም ቡድኖች የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እየተቀባበሉ የምስጋና መዝሙር በማቅረብ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሻብያ፥ ሼሬብያ፥ የቃድሚኤል ልጅ ኢያሱና ወንድሞቻቸው ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ክፍል በክፍል ትይዩ ሆነው ያወድሱና ያመሰግኑ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሌዋውያኑም አለቆች አሳብያ፥ ሰርብያ፥ ኢያሱ፥ የቀድምኤልም ልጆች፥ ወንድሞቻቸውም እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በእነርሱ ፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሌዋውያኑም አለቆች ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር። |
በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ሆነው ምስጋና፥ ውዳሴና ክብር በማቅረብ ለእግዚአብሔር አምላክ የሚደረገውን የአምልኮ ሥነ ሥርዓት እንዲመሩ ዳዊት ጥቂት ሌዋውያንን ሾመ።
አባቱ ዳዊት የደነገጋቸውን መመሪያዎች በመከተልም የካህናቱንና ካህናቱን በሥራና መዝሙር በመዘመር የሚረዱትን ሌዋውያን የየዕለቱን የሥራ መደብ አቀናበረ፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የቤተ መቅደሱ ዘበኞች በእያንዳንዱ ቅጽር በር የዕለት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አከፋፍሎ መደበ።
ከምርኮ የተመለሱት የሌዋውያን ቤተሰቦች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የሆዳውያ ዘሮች የሆኑት የኢያሱና የቃድሚኤል ቤተሰቦች 74 የአሳፍ ዘሮች የሆኑት የቤተ መቅደስ መዘምራን ብዛት 128 የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች የሆኑት የሻሉም፥ የአጤር፥ የጣልሞን፥ የዓቁብ፥ የሐጢጣና የሾባይ ዘሮች 139
ማታንያ የሚካ ልጅ፥ የዘብዲ ልጅ፥ የመዘምራን አለቃ የነበረው የአሳፍ ልጅ፥ የእርሱ ምክትል የነበረው የባቅቡቅያ ልጅና፥ የሻሙዐ ልጅ የነበረው ዐብዳ፥ የጋላል ልጅ፥ የዩዱቱን ልጅ፥
ይሁን እንጂ የሌዋውያን ቤተሰብ አለቆች በግልጽ መዝገብ የታወቁት የኤልያሺብ የልጅ ልጅ የሆነው ዮናታን በሕይወት እስከ ኖረበት ዘመን ብቻ ነበር።
የራሱ ጐሣ አባላት የነበሩት ሸማዕያ፥ ዐዛርኤል፥ ሚለላይ፥ ጊለላይ፥ ማዓይ፥ ናትናኤል፥ ይሁዳና ሐናኒ የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ይዘምርበት የነበረውን የሙዚቃ መሣሪያ ሁሉ ተሸክመው ተከተሉት፤ የዚህንም ቡድን ሰልፍ የሚመራው የሕግ ሊቁ ዕዝራ ነበር።
ከዚህ በኋላ ተነሥተው ባሉበት ስፍራ ቆሙ፤ ከዚህ ቀጥሎ ስማቸው የተዘረዘረ ሌዋውያንም የሕጉን መጽሐፍ ትርጒም ለሕዝቡ አብራሩላቸው፤ እነርሱም ኢያሱ፥ ባኒ፥ ሼሬብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሻበታይ፥ ሆዲያ፥ መዕሤያ፥ ቀሊጣ፥ ዐዛርያስ፥ ዮዛባድ፥ ሐናንና ፐላያ ነበሩ።
ለሌዋውያኑ መቆሚያ መድረክ ነበር፤ በዚያም ላይ ኢያሱ፥ ባኒ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ቡኒ፥ ሼሬብያ፥ ባኒና ከናኒ በመቆም፥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ጸለዩ።
የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከዚህ ሁሉ ሽሽ፤ ጽድቅን፥ መንፈሳዊነትን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ በትዕግሥት መጽናትን፥ ገርነትን ተከታተል።
አንድ ቀን ከይሁዳ ነገድ የሆኑ ሰዎች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ከእነርሱ አንዱ የቀኒዛዊው የይፉኔ ልጅ ካሌብ እንዲህ አለው፦ “በቃዴስ በርኔ በነበርንበት ጊዜ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ስለ አንተና ስለ እኔ የተናገረውን ታውቃለህ፤