Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 12:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በቤተ መቅደሱ ቅጽር በር አጠገብ የተሠሩትን የዕቃ ግምጃ ቤቶች የሚጠብቁ ዘበኞችም ማታንያ፥ ባቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ መሹላም፥ ጣልሞንና ዓቁብ ተብለው የሚጠሩት ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በቅጥሩ በሮች አጠገብ ያሉትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁት ዘቦች ደግሞ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም፣ ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ማታንያ፥ ባቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ ምሹላም፥ ጣልሞን፥ ዓቁብ በበሮቹ አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች የሚጠብቁ በር ጠባቂዎች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 መታ​ንያ፥ በቅ​ቡ​ቅያ፥ አብ​ድያ፥ ሜሱ​ላም፥ ጤል​ሞን፥ ዓቁብ በበ​ሮች አጠ​ገብ የሚ​ገ​ኙ​ትን ዕቃ ቤቶች ለመ​ጠ​በቅ በረ​ኞች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 መታንያ፥ በቅቡቅያ፥ አብድዩ፥ ሜሱላም፥ ጤልሞን፥ ዓቁብ በበሮች አጠገብ የሚገኙትን ዕቃ ቤቶች ለመጠበቅ በረኞች ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 12:25
10 Referencias Cruzadas  

ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።


እንዲሁም እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ቤተ መቅደሱን የመንከባከብ ኀላፊነት የእነርሱ ነበር፤ በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚፈጸመው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዘመዶቻቸውን የአሮን ዘሮች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር።


የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎች በየቤተሰቡ በቡድን ተከፍለው ነበር፤ እነርሱም ልክ እንደ ሌሎቹ ሌዋውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገልግሎት ነበራቸው፤


ለዖቤድኤዶም በደቡብ በኩል የሚገኘው ቅጽር በር ደረሰው፤ ልጆቹም የዕቃ ግምጃ ቤቶችን ለመጠበቅ ተመደቡ፤


በየቀኑ በምሥራቅ በኩል ስድስት፥ በሰሜን አራት፥ በደቡብ አራት ዘብ ጠባቂዎች ይመደባሉ፤ እንዲሁም በየቀኑ አራት ዘብ ጠባቂዎች የዕቃ ግምጃ ቤቶቹን ለመጠበቅ ሲመደቡ፥ ከእነርሱ ሁለቱ አንዱን የዕቃ ግምጃ ቤት፥ ሁለቱ ደግሞ ሌላውን ይጠብቁ ነበር።


አባቱ ዳዊት የደነገጋቸውን መመሪያዎች በመከተልም የካህናቱንና ካህናቱን በሥራና መዝሙር በመዘመር የሚረዱትን ሌዋውያን የየዕለቱን የሥራ መደብ አቀናበረ፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ባዘዘው መሠረት የቤተ መቅደሱ ዘበኞች በእያንዳንዱ ቅጽር በር የዕለት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ አከፋፍሎ መደበ።


ዘብ ጠባቂው “ጌታዬ ሆይ! እኔ በማማዬ ላይ ሆኜ ሌት ከቀን በመጠበቅ ላይ ነኝ” ይላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos