Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 12:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑም አለ​ቆች አሳ​ብያ፥ ሰር​ብያ፥ ኢያሱ፥ የቀ​ድ​ም​ኤ​ልም ልጆች፥ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእ​ዛዝ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው በእ​ነ​ርሱ ፊት ያከ​ብ​ሩና ያመ​ሰ​ግኑ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሸብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድምኤል ልጅ ኢያሱ ነበሩ፤ እነርሱም ከወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት እየተቀባበሉ ውዳሴና ምስጋና ያቀርቡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የሌዋውያኑ መሪዎች ሐሻብያ፥ ሼሬብያ፥ የቃድሚኤል ልጅ ኢያሱና ወንድሞቻቸው ደግሞ ከፊት ለፊታቸው ሆነው የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ክፍል በክፍል ትይዩ ሆነው ያወድሱና ያመሰግኑ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ሌዋውያኑ በሐሻብያ፥ በሼሬብያ፥ በኢያሱ፥ በቢኑይና በቃድሚኤል መሪነት በሁለት ቡድኖች ተከፈሉ። ሁለቱም ቡድኖች የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ንጉሥ ዳዊት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እየተቀባበሉ የምስጋና መዝሙር በማቅረብ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የሌዋውያኑም አለቆች ሐሸብያ፥ ሰራብያ፥ የቀድምኤልም ልጅ ኢያሱ እንደ እግዚአብሔር ሰው እንደ ዳዊት ትእዛዝ በየሰሞናቸው በወንድሞቻቸው ፊት ለፊት ያከብሩና ያመሰግኑ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 12:24
18 Referencias Cruzadas  

ሴቲ​ቱም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በአ​ፍህ እው​ነት እንደ ሆነ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ​ችው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያወ​ድ​ሱት ዘንድ፥ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ትና ያከ​ብ​ሩ​ትም ዘንድ ከሌ​ዋ​ው​ያን ወገን አቆመ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ዳዊት እን​ዲህ አዝዞ ነበ​ርና ካህ​ና​ቱን እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሥር​ዐት በየ​አ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ሰሞን ከፈ​ላ​ቸው፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ያመ​ሰ​ግኑ ዘንድ፥ በካ​ህ​ና​ቱም ፊት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው፤ በረ​ኞ​ቹ​ንም ደግሞ በየ​በሩ ሁሉ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ከፈ​ላ​ቸው።


ሌዋ​ው​ያኑ፤ ከሁ​ድያ ልጆች ወገን የኢ​ዮ​ስ​ስና የቀ​ዳ​ም​ሔል ልጆች ሰባ አራት።


በጸ​ሎ​ትም ጊዜ ምስ​ጋ​ናን የሚ​ጀ​ምሩ አለ​ቃው የአ​ሳፍ ልጅ፥ የዛ​ብዲ ልጅ፥ የሚካ ልጅ ማታ​ንያ፥ በወ​ን​ድ​ሞ​ቹም መካ​ከል ሁለ​ተኛ የነ​በረ ቦቂ​ቦ​ቅያ፥ የኢ​ዶ​ትም ልጅ፥ የጌ​ላል ልጅ፥ የሰ​ሙዓ ልጅ አብ​ድያ።


የሌዊ ልጆች የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች እስከ ኤል​ያ​ሴብ ልጅ እስከ ዮሐ​ናን ዘመን ድረስ በታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጻፉ።


ወን​ድ​ሞ​ቹም ሰማ​ዕያ፥ አዘ​ር​ኤል፥ ማዕ​ላይ፥ ጌላ​ላይ፥ መዓይ፥ ናት​ና​ኤል፥ ይሁዳ፥ አናኒ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው የዳ​ዊ​ትን የዜ​ማ​ውን ዕቃ ይዘው ሄዱ፤ ጸሓ​ፊ​ውም ዕዝራ በፊ​ታ​ቸው ነበረ።


ደግሞ ኢያ​ሱና ባኒ፥ ሰራ​ብያ፥ ያሚን፥ ዓቁብ፥ ሳባ​ታይ፥ ሆዲያ፥ መዕ​ሤያ፥ ቆሊጣ፥ ዓዛ​ርያ፥ ኢዮ​ዛ​ባድ፥ ሐናን፥ ፌል​ዕያ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ሕጉን ለሕ​ዝቡ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸው ቆመው ነበር።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም ኢያ​ሱና የቀ​ድ​ም​ኤል ልጆች፥ የሰ​ራ​ብያ ልጅ ሴኬ​ንያ፥ የከ​ናኒ ልጆ​ችም በደ​ረ​ጃ​ዎች ላይ ቆመው ወደ አም​ላ​ካ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በታ​ላቅ ድምፅ ጮኹ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሙሴ ሳይ​ሞት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የባ​ረ​ከ​ባት በረ​ከት ይህች ናት።


አንተ ግን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።


የይ​ሁ​ዳም ልጆች በጌ​ል​ገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔ​ዛ​ዊ​ውም የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአ​ም​ላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃ​ዴስ በርኔ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታው​ቃ​ለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos